askwala.com - ታዋቂው ናይጄሪያዊ ሰባኪ ቲቢ ጆሽዋ አረፉ
Header







ታዋቂው ናይጄሪያዊ ሰባኪ ቲቢ ጆሽዋ አረፉ

Image name: TB joshua.png

ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሽዋ ቅዳሜ ዕለት ህይወታቸው አልፏል።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሽዋ ማረፋቸውንም ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ "አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል" በሚልም ሰፍሯል። ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል። በተከታዮቻቸውም ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሽዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ።
በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል። 

















Short info

× Chat