askwala.com - በህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች የኮምፒውተር አጠቃቀማችን በምን መልኩ ሊሆን ይገባል?
Header







በህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች የኮምፒውተር አጠቃቀማችን በምን መልኩ ሊሆን ይገባል?


ኮምፒውተሮችን፣ ስማርት ስልኮችን ወይም ታብሌቶችን ህዝብ በሚበዛባቸዉ ስፍራዎች ላይ መጠቀም በመኖሪያ ቤት ወይም በቢሮ ውስጥ የመጠቀም ያክል እየተለመዱ መጥተዋል፡፡ የራስዎን መሣሪያዎች ይሁን በኢንተርኔት ካፌ ወይም በቤተመፅሐፍት ውስጥ በሚያገኟቸውን ኮምፒውተሮች ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ የሚጠቀሙ ከሆነ በርካታ የደህንነት ስጋቶች ሊያጋጥምዎ ይችላል፡፡
ከእነዚህም ስጋቶች መካከል፡-
• ደህንነቱ ያልተጠበቀ እና ሕገ-ወጥ ገመድ አልባ ኢንተርኔት (wifi) የሚጠቀሙ ከሆነ የኦንላይን እንቅስቃሴዎን የሚከታተሉ ሰዎች ሊኖሩ መቻላቸው፤
• ከጀርባዎ ተቀምጠው የሚጠቀሙቧቸውን መሣሪያዎች ስክሪን የሚቃኙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤
• ኮምፒውተርዎ፣ ስማርት ስልኮ ወይም ታብሌቶ ሊጠፉ ወይም ሊሰረቁ ይችላሉ፤
• እንደስፓይዌር /Spyware/ ያሉ አጥፊ ሶፍትዌሮች በህዝብ ኮምፒውተሮች ላይ ሊያጋጥምዎት ይችላል፤
• በህዝብ ኮምፒውተሮች ሲጠቀሙ የግል መረጃዎችዎ መሰረቅ ወይም መረጃ ያሰሱበት ማፈላለጊያ (browser) ታሪክ ሊቃኝቦት ይችላል፡፡
ስለዚህ በህዝብ የጋራ መጠቀሚያ በሆኑ ኮምፒውተሮች ወይም ህዝብ በበዛባቸዉ ስፍራዎች ስንጠቀም፡-
• እንደ ክሬዲት ካርድ ቁጥሮች ያሉ ጠቃሚ የይለፍ-ቃሎችን ወይም የግል መረጃዎችን ሊያሳዩ የሚችሉ የገንዘብ ግብይቶችን ያስወግዱ፤
• በተቻለ አቅም እምነት የማይጣልባቸው የህዝብ ኮምፒውተሮችን ከመጠቀም በፊት ሰላይ አጥፊ ሶፍትዌሮችን /Spyware/ ለመፈተሽ ወይም ለመቃኘት ታማኝ የድር አጥፊ ሶፍትዌሮች ማጽጃ ፕሮግራሞችን ይጠቀሙ፤
• በይነ-መረብ እየተጠቀሙ ከነበረ ፋይሎችን እና ኩኪዎችን /Cookies/ የሚሰርዝ ማፈላለጊያ መጠቀምዎን እና ቅኝት ያደረጉበትን ማፈላለጊያ ታሪክ ማጽዳቶን ያረጋግጡ፤
• የኢንተርኔት አማራጭ የሚያፈላልጉባቸውን እና የሚጠቀሙባቸውን ማናቸውም የይለፍ -ቃላት ደህንነት ይጠብቁ፤ ጥርጣሬ ካለዎት የማፈላለጊያውን እገዛ አማራጭ ይጠቀሙ፤
• ወደ ቤትዎ ከተመለሱ በኋላ በህዝብ ኮምፒውተር ላይ የተጠቀሙባቸውን ማናቸውም ዓይነት የይለፍ-ቃላት መቀየር እንዳለብዎት አይዘንጉ፡፡
• እንደ Gmail፣ Hotmail ወይም Yahoo ያሉ የድር መልዕክት መለዋወጫ አካውንት የሚጠቀሙ ከሆነ እና የተላከልዎን መልእክት (ኢ-ሜይልዎን) ለማየት ከፈለጉ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የድር አገናኝ /web link/ መጠቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ፤
• ከበስተጀርባዎ ቆመው የሚጠቀሙትን መረጃ የሚመለከቱ ሰዎች አለመኖራቸውን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ 

















Short info

× Chat