askwala.com - ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለዊንዶዉስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች የደህንነት ማዘመኛዎችን አቀረበ
Header







ማይክሮሶፍት ኩባንያ ለዊንዶዉስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች የደህንነት ማዘመኛዎችን አቀረበ


ማይክሮሶፍት ኩባንያ ዊንዶዉስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች የደህንነት ማዘመኛዎችን ማቅረቡን ገለጸ፡፡
ኩባንያዉ 50 ለሚሆኑ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ክፍተቶች የሚሆኑ መጠገኛዎችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህ መጠገኛዎች መካከል 6 የሚሆኑት ቀድመዉ ያልተለዩ እና ጥቃት ሲያደርሱ የነበሩ መሆናቸዉን ኩባንያዉ ጠቁሟል፡፡
በኩባንያዉ ተለይተዉ የደህንነት ጥገና ከተደረገላቸዉ ሲስተሞች መካከልም ኔት ኮር እና ቪዡዋል ስቱዲዮ (NET Core and Visual Studio) ፣ ማይክሮሶፍት ኦፊስ (Microsoft Office) ፣ ማይክሮሶፍት ኤጅ (Microsoft Edge) ፣ ሼር ፖይንት ሰርቨር (Share Point Server) ይገኙበታል፡፡
እንደ ማይክሮሶፍት የአደገኝነት ደረጃ ምዘና ከ50ዎቹ ተጋላጭነቶች ዉስጥ 5ቱ 'እጅግ አደገኛ' የሚል ደረጃዎችን የሰጣቸዉ ሲሆን 45ቱንደግሞ 'አደገኛ' በሚል አስቀም አስቀምጧቸዋል፡፡
በመሆኑም የማይክሮሶፍት ዊንዶዉስ ተጠቃሚዎች ኩባንያዉ ያቀረበዉን የደህንነት ዝመና ለመተግበር "Start" የሚለዉን በመጫን “Settings” በመምረጥ “Update እና Security” የሚለዉን መጫን በመጨረሻም “Windows Update” ወይም “Check for Windows updates” የሚለዉን በመጫን የማይክሮሶፍት ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ከፍተት መድፈን ይችላሉ፡፡ 

















Short info

× Chat