askwala.com - አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፌስቡክ የግሩፕ/ቡድን መጠቀሚያ ላይ እየተሞከረ ነው
Header







አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፌስቡክ የግሩፕ/ቡድን መጠቀሚያ ላይ እየተሞከረ ነው


በፌስቡክ ግሩፖች የሚደረጉ ውይይቶች አንዳንዴ ፈር እየለቀቁ የስድብ እና ጥላቻ መድረክ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ ፌስቡክ መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን ከሰሞኑ በሙከራ ደረጃ ስራ ላይ ማዋሉ ተሰምቷል፡፡
በግሩፕ መጠቀሚያዎች ውስጥ ከሚደረገው ውይይት የጭቅጭቅ መንፈስ ያላቸውን እና ጤናማ ያልሆኑ ውይይቶችን የአርቲፊሻል ኢንለተለጀንስ ስልተቀመሩ በመለየት ቡድኑን ወደሚያስተዳድሩት ሰዎች የግጭት ማስጠንቀቂያ እንደሚልክ ሲ.ኤን.ኤን አስነብቧል፡፡
ማስጠንቀቂያው የደረሰው የቡድኑ አስተዳዳሪም ግጭቱ ሳይባባስ በፍጥነት ማብረድ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ ይችላል፡፡
በዓለም ዙሪያ 2.8 ቢሊዮን ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስቡክ በትስስር ድረ-ገጹ 70 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ግሩፕ ፈጥረው እንደሚያስተዳድሩ ገልጿል፡፡
በማሕበራዊ ትስስር ድረ-ገጹ ላይ በአስር ሚሊዮኖች የሚጠጉ ግሩፖች እንዳሉና በቡድኖቹ ውስጥ 1.8 ቢሊዮን ሰዎች በየወሩ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ዘገባው አስታውሷል፡፡ 

















Short info

× Chat