askwala.com - ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ግንኙነት ሽፋን በስታርሊንክ ሳተላይት
Header







ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ግንኙነት ሽፋን በስታርሊንክ ሳተላይት


በስፔስ ኤክስ እየተገነባ የሚገኘው ስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔት ሥርዓት በመስከረም ወር አካባቢ የማይቋረጥ የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚችል አስታወቀ፡፡
የአንድ ሺህ ስምንት መቶ ሳተላይቶች ስምሪት በስኬት መጠናቀቁን እና እስከ መጪው መስከረም ወር ተልዕኳቸውን ተግባራዊ ወደሚያደርጉበት ምህዋር እንደሚደርሱ የስፔስ ኤክስ ፕሬዝደንት ግዌን ሾትዌልን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
ይሁንና ይህን አገልግሎት ለሁሉም ሀገራት ለማቅረብ በየሀገራቱ የአሰራር ሕግ መሰረት ፍቃድ ሊያገኝ እንደሚገባ ፕሬዝደንቷ ገልጸዋል፡፡
ስታርሊንክ የሳተላይት ኢንተርኔትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ በስፔስ ኤክስ ኩባንያ እየተገነባ ያለ ብዛት ያላቸው አነስተኛ ሳተላይቶች (ሕብረ-ሳተላይት) ጥምር መሆኑ ይታወቃል፡፡ 

















Short info

× Chat