askwala.com - ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ሶፍትዌር አበልጻጊዎችን ማገዝ
Header







ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ሶፍትዌር አበልጻጊዎችን ማገዝ


ንብረትነቱ የማይክሮሶፍት ኩባንያ የሆነው ጊትሃብ (GitHub) ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ሶፍትዌር የሚያበለጽጉ ሰዎችን ለማገዝ እየሰራ እንደሆነ ተሰማ፡፡ ጊትሃብ የተለያዩ ኮዶችን የሚያጋራ አገልግሎት ሲሆን በቅርብ GitHub Copilot የተሰኘ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ ሶፍትዌር ለማበልጸግ የሚረዳ አገልግሎትን አስተዋውቋል፡፡
ይፋ የተደረገው አገልግሎት ሶፍዌር ለማበልጸግ የሚረዱ አንዳንድ ቴክኒካዊ ክህሎቶችን የሚያጋራ ሲሆን የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችሉ ገለጻዎችም ታክለውበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በኮዶች መካከል ያለውን ልዩነት፣ የተለያዩ መተግበሪያዎችን የአፈጻጸም ብቃት መከታተል እና ጊዜንና ገንዘብል በአግባቡ ለመጠቀም የሚረዱ መግለጫዎችንም አካትቶ የቀረበ ነው፡፡ ምርምሮች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ዘርፉ በአሁኑ ሰዓት 1.5 ቢሊዮን ዶላርን በየአመቱ ያንቀሳቅሳል፡፡
ጊትሃብ እንደሚለው ከሆነ ለሶፍትዌር አበልጻጊዎች የቀረበው ይህ አገልግሎት የአበልጻጊዎችን ቀደምት ስራዎች በመተንተንና ተዛማጅ የሆኑ እገዛዎችን በማቅረብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አገልግሎቱ መሰረቱን በሲልከን ቫሊ ባደረገ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የምርምር ተቋም እና በጊትሃብ ትብብር የቀረበ ሲሆን የምርምር ተቋሙ በቢሊዮን የሚቆጠሩ እና በጊትሃብ የሚተዳደሩ የተለያዩ የኮድ መስመሮችን የሚጠቀም ነው፡፡ ማክሮሶፍት ለተመሳሳይ አገልግሎት ለጊትሃብ በ2018 የ7.5 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ መክፈሉ የሚታወስ ነው፡፡ 




© Forbes   













Short info

× Chat