askwala.com - 130 ሀገራትን ያካተተ ዓለም አቀፍ የግብር ስምምነት ተደረሰ
Header







130 ሀገራትን ያካተተ ዓለም አቀፍ የግብር ስምምነት ተደረሰ

Image name: us-digital-giants-are.jpg

130 ሀገራት ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተገቢውን ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ የግብር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ፡፡ የምጣኔ ሐብት ትብብርና ልማት ድርጅት (OECD) ባስታወቀው መሰረት ስምምነቱ እንደ ጉግል፣ አማዞን፣ ፌስቡክ እና አፕል ያሉት ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ከአሁን በኋላ በየሄዱበት ቢያንስ የ15 በመቶ ግብርን እንዲከፍሉ የሚያደርግ ሲሆን ይህም ለሀገራቱ መንግስታት የ150 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገቢን እንደሚያስገኝላቸው ይጠበቃል፡፡ ሆኖም በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ያሉ ሀገራት የስምምነቱ አካል ለመሆን አልፈቀዱም፡፡
በሀገራቱ መካከል የተደረሰው ስምምነት ሳምንታትን አስቀድሞ በባለፀጎቹ የቡድን 7 አባል ሀገራትን ፊት ቡራኬን መቀበሉ ሲዘገብ በቀጣይም ከቀናት በኋላ የጣልያኗ ቬኒስ ውስጥ በሚከናወነው የቡድን 20 ሀገራት ላይ እንደሚቀርብም ይጠበቃል፡፡ የአሜሪካን ፕሬዘዳንት ጀ ባይደን ስምምነቱ ሀገራት የኮርፖሬት ታክስን በከፍተኛ ደረጃ ለማውረድ የሚያርጉትን ፉክክር ስለማስቆሙና ሀገራቸው ያላት ተወዳዳሪነትንም ከፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ጀርመንም በበኩሏ ወደ ፍትሀዊ ግብር የተደረገ ታላቅ እርምጃ ስትል አወድሳዋለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ስምምነቱ በተለይም እንደ አየርላንድ ሉክሰንበርግ፣ ፖላንድ እና ሀንጋሪ ያሉት አነስተኛ የግብር መጠን ያላቸውና ይህንንም ተጠቅመው ኩባንያዎችን የሚስቡ የአውሮፓ ህብረት መንግስታት አልተቀበሉትም፡፡ እንደ ፌስቡክ፣ ጉግል እና አፕል ላሉት ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መቀመጫ የሆነችው አየርላንድ የኮርፖሬት ግብር መጠኗ 12.5 በመቶ ላይ የፀና ነው፡፡ የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስትር ፓስካል ዶኖሆ እንደሚሊት መሰል ሁሉን አቀፍ ስምምነት አስፈላጊ ቢሆንም የ15 በመቶ ግብር ስምምነትን መፈረም ግን አየርላንድ ከኮርፖሬሽኖች ከምታገኘው ገቢ ውስጥ 20 በመቶ የሚሆነውን እንድታጣ ሊያደርጋት ይችላል ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በአጠቃላይ ስምምነቱ ላይ ተቀምጠው ከነበሩ 139 ሀገራት መካከልም ሳይስማሙ የቀሩት ቁጥር ዘጠኝ ሆኗል፡፡ 




© Tech Xplore   













Short info

× Chat