askwala.com - የተሳካው የቢሊየነሩ ሪቻርድ ብራንሰን የሕዋ ጉዞ
Header







የተሳካው የቢሊየነሩ ሪቻርድ ብራንሰን የሕዋ ጉዞ

Image name: space tourism.PNG

እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ሪቻርድ ብራንሰን በኩባንያው በተሰራች ዩኒቲ ሮኬት አውሮፕላን ወደ ሕዋ መዳረሻ ያደረገው ጉዞ በስኬት ተጠናቋል፡፡
ቢሊየነሩን ጨምሮ አምስት ሰዎችን ይዛ የተጓዘችው የሮኬት አውሮፕላን ከምድር ተነስታ ወደ ሰማይ 15 ኪ.ሜ ርቀት እስክትደርስ ባለ መንታ አካል ግዙፍ ጄት መሀል እንድትጣበቅ ተደርጓል፡፡
ተፈላጊው ከፍታ ላይ እንደደረሱ በሮኬት አውሮፕላኗ የኋለኛው ክፍል የተገጠመው የሮኬት ሞተር በመቀጣጠል እና አውሮፕላኗን ከሚሸኛት ግዙፍ ጄት በማላቀቅ ወደ ሕዋ መዳረሻ አስወንጭፏታል፡፡
ከምድር 85 ኪ.ሜትሮችን ርቃ መብረር የቻለችው የሮኬት አውሮፕላን አንድ ሰዓት የፈጀው ሙሉ የጉዞ ሂደቷን አጠናቃ ተሳፋሪዎቿን ይዛ በሰላም ማረፍ ችላለች፡፡
ዩኒቲ የተባለችው የሮኬት አውሮፕላን ላለፉት 17 ዓመታት በቢሊየነሩ ኩባንያ ቨርጂን ጋላክቲክ ውስጥ ስትሰራ መቆየቷን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ለሕዋ ቱሪዝም አዲስ በር ከፋች እንደሆነ ለተነገረለት የደርሶ መልስ ጉዞ ስድስት መቶ ሰዎች ተመዝግበው ወረፋ እየጠበቁ ሲሆን የጉዞ ትኬቱ ዋጋ በሰው 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡ 

















Short info

× Chat