askwala.com - በጉግል የበለፀገው አዲሱ የማሽን ለርኒንግ ሥርዓት ብዛት ያላቸው ተግባራትን ማከናወን እንደሚችል ተገለፀ፡፡
Header







በጉግል የበለፀገው አዲሱ የማሽን ለርኒንግ ሥርዓት ብዛት ያላቸው ተግባራትን ማከናወን እንደሚችል ተገለፀ፡፡


በጉግል ባለቤትነት የሚተዳደረው እና መቀመጫውን በሀገረ እንግሊዝ ያደረገው ዲፕማይንድ የተባለው ተቋም የተለያዩ አይነት ዳታዎችን በግብዓትነት የሚጠቀም እና በውጤቱም ብዙ ተግባራትን ማከናወን የሚችል የማሽን ለርኒንግ ሥርዓት አሰተዋውቋል፡፡
ፐርሲቨር ተብሎ የተሰየመው ሥርዓት ምስል፣ ቪዲዮ እና መልክአምድራዊ ዳታዎችን በግብዓትነት መጠቀም እንደሚችል የዜድኔት ዘገባ አመላክቷል፡፡
እስካሁን በነበረው የማሽን ለርኒንግ ሥርዓት ለተለያዩ አይነት ዳታዎች ለእያንዳንዳቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት አውታረ መረቦችን ማበልፀግ ይጠይቅ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ፐርሲቨር ይህን በማስቀረት በዘርፉ አብዮት እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
ይህ አዲስ ሥርዓት በትንሽ ዳታና በአጭር ጊዜ ብዙ መማር የሚችል እንዲሁም ብዛት ያላቸው ተግባራትን በማከናወን በዘርፉ የሚደረገውን ጥናት እና ምርምር አንድ እርምጃ ወደፊት የወሰደ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ 

















Short info

× Chat