askwala.com - አፕል በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የህጻናት ፆታዊ ጥቃት መከታተያ ሲስተም ተከላከለ
Header







አፕል በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የህጻናት ፆታዊ ጥቃት መከታተያ ሲስተም ተከላከለ

Image name: Apple.jpg

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት አፕል ህፃናት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ያስችላል ያለውን በደንበኞች ስልክ የሚጫን የመከታተያ ሲሲተም ማስተዋወቁ አይዘነጋም፡፡ በአፕል ውሳኔ ተግባር ላይ ይውላል የተባለው ይህ ሲስተም ከህፃናት ጋር ተያይዞ ማንኛውም ቨርቺዋል የፆታዊ ጥቃት የሚያሳዩ ነገሮችን (CSAM) ለመከላከል የታሰበ ቢሆንም ብዙ አካላት ይህ ሲስተም የፕራይቬሲ መብትን፣ አላስፈላጊ ስላላዎችን እና በቴክኖሎጂ የተደገፉ ወንጀሎች በተጠቃሚዎች ላይ ሊያስከትል ይችላል በሚል ተቃውሞ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡
ይሁንና ድርጅቱ አፕል በደንበኞች የኦፐሬቲን ሲስተም ላይ ይጫናሉ ያላቸው እነዚህ የህጻናት ፆታዊ ጥቃት መከታተያ ሲስተሞች ልጆችን ለመከላከል ከመዋላቸው እኩል የተጠቃሚዎችን የፕራይቬሲ መብት ለመጠበቅ ምንም እንደማያግዳቸው አስታውቋል፡፡ ኒውራልሃሽ (NeuralHash) በሚል የተሰየመው አዲሱ የመከታተያ ቱል በኤፎን ላይ የተቀመጡ ማንኛውም ቨርቺዋል የፆታዊ ጥቃት የሚያሳዩ ምስሎችን ወይም ነገሮችን ፋይሉን ዲክሪፕት ሳያደርግ ለመለየት የሚችል ሲሆን እንደ ጎግል ማክሮሶፍት እና ድሮፕቦክስ ያሉ ግዙፍ የክላውድ አገልግሎት አቅራቢዎች ይህንን የመለየት ወይም ስካን የማድረግ ተግባር በራሳቸው ሲስተም እየሰሩበት ይገኛል፡፡
ይሁንና አፕል ያቀረበው አዲስ ሲሰተም ከሌሎቹ ለየት የሚደርገው ማንኛውም ቨርቺዋል የፆታዊ ጥቃት የሚያሳዩ ምስሎችን ወይም ነገሮች ወደ ክላውድ ከመግባታቸው በፊትም በራሱ በሰዎች የኤፎን መሳሪያ ላይ ስካን ሊደረግ መቻለቸው ውዝግቡ እንዲነሳ ያደረገ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ክርክር እስካሁን ከ5,000 የሚበልጡ ሰዎች እና ተቋማት በተጠቃሚዎች ላይ ስለላ ለማካሄድ የሚያስችል ትግበራ ነው በሚል የድርጅቱን ውሳኔ የሚቃወም ፊርማ አሰባስበዋል፡፡
አፕል ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው የመከታተያ ቱል በዚህ አመት ማዘመኛ በሚደረግላቸው iOS 15, iPadOS 15 እና ሌሎች የኦፕሬቲን ሲሰተሞች ላይ የሚካተቱ ቢሆንም ከብዙ ግለሰቦች እና ተቋማት እየተሰማ ያለው የተቃውሞ ድምጽ ድርጅቱ ይህን ውሳኔውን መልሶ እንዲቃኘው እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲፈልግ የሚያስገድደው ነው ተብሏል፡፡ 




© Technologyreview   













Short info

× Chat