askwala.com - በኖኪያ የቀረበ ነጻ የትምህርት እድል
Header







በኖኪያ የቀረበ ነጻ የትምህርት እድል

Image name: Udacity Scholarships.jpg

የፊንላንዱ የቴሌኮም እና የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች አምራች ኩባንያ ኖኪያ ብላክስ ኢን ቴክኖሎጂ (BIT Foundation) ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ነጻ የድረ-ገጽ የትምህርት እድል አቀረበ፡፡
የትምህርት እድሉ በቴክኖሎጂው ዘርፍ አነስተኛ ውክልና ላላቸው ማህበረሰቦች የተሻለ እድል ለመስጠት ያለመ ነው፡፡
Udacity በተባለው የድረ-ገጽ የትምህርትና የክህሎት ማሻሻያ መድረክ አማካኝነት የሚቀርቡት የትምህርት አይነቶች #Artificial_Intelligence፣ #Programming_and_Development እና #Cloud_Computing ዙሪያ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡
የማመልከቻ ጊዜው እስከ አውሮፓውያኑ መስከረም 27፤ 2021 እንደሚቆይ ታውቋል፡፡
እርስዎም በተጠቀሱት የትምህርት አይነቶች እውቀት እና ክህሎትዎን የማዳበር ፍላጎት ካለዎት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማመልከት ይችላሉ፡፡ 

















Short info

× Chat