askwala.com - ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የኤች አይ ቪ ክትባት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ
Header







ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የኤች አይ ቪ ክትባት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ


በጆንሰን እና ጆንሰን ተሰርቶ በአፍሪካ ለሙከራ የቀረበው የኤች አይ ቪ ክትባት ወጣት ሴቶችን በበቂ መጠን ከቫይረሱ መጠበቅ ሳይቻለው ቀርቷል፤ ይህም ለቫይረሱ መከላከያ ክትባት ለማግኘት እየተደረገ ባለው ርብርብ ላይ ጥላውን አጥልቷል፡፡ ሆኖም ድርጅቱ የክትባቶቹን ውጤታማነትና ደህንነት በወንዶች ላይ መሞከሩን እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡ በአውሮፓ እንዲሁም በሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛው አሜሪካን የሚደረጉት ሙከራዎችም ከሦስት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በአውሮፓውያኑ 2024 እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡
ኢምቦኮዶ የተሰኘውና ገና መቋጫውን ያላገኘው ይህ የጆንሰን እና ጆንሰን ኤች አይ ቪ ክትባትን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተደረገ ጥናት በኤች አይ ቪ ከሚያዙ አዳዲስ ሰዎች መካከል ከ60 በመቶ የሚልቁት ሴቶችና ህፃናት በሆኑባቸው ከአምስት የተለያዩ የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 2,600 ሴቶችን አካቶ የተከናወነ ነው፡፡ በጥናቱ ላይ ታድያ የኤች አይ ቪ ክትባቱ ያሳየው ውጤታማነት 25.2 ብቻ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በየዓመቱ የ680,000 ሰዎች ህይወትን የሚቀጥፈው የኤድስ በሽታን የመያስከትለው ይህ የኤች አይ ቪ ቫይረስን በመዋጋት ረገድ በቫይረሱ የተጠቁ ወገኖች የበሽታ መከላከያ ስርዓትን ጠብቆ የሚያቆይ ህክምና በውጤታማነት እየተሰጠ ቢሆንም ቫይረሱን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ግን የክትባት አስፈላጊነት የማያጠያይቅ ነው፡፡
በጥናቱ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአሜሪካን ብሔራዊ የአለርጂና ተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲትዩት ዳይሬክቴሩ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ “ምንም እንኳን የይህ ውጤት ተስፋ ያደረግነው ባይሆንም ከኢምቦኮዶ ጥናት የተቀሰሙ እውቀቶችን መጠቀም ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እርሳቸው በሚመሩት ኢንስቲትዩት እንዲሁም በቢልና ሜሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን አማካኝነት ድጋፍ ይደረግለት የነበረው የኢምቦኮዶ ጥናት ጆንሰን እና ጆንሰን እንደሚያመርታቸው የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቶች ሁሉ የተዳከመ ቫይረስን የሚጠቀም ነው፡፡
በወራት ጊዜ ውስጥ ሌላኛው የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ሞደርና የኤምአርኤንኤ ኤች አይ ቪ ክትባቶችን በሰዎች ላይ መሞከር የሚጀምር ሲሆን ሌሎች ጥናቶችም እንዲሁ በአፍሪካ ውስጥ የተለያዩ አይነት የኤች አይ ቪ መከላከያ ክትባቶችን እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡ 




© ሮይተርስ   













Short info

× Chat