askwala.com - የሰዶም እሳት
Header







የሰዶም እሳት


በመፅሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 19 ላይ ከሰማይ በዘነበ እሳት አማካኝነት የሰዶም እና ገሞራ ከተሞች መጥፋታቸው ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ታድያ አዲስ የወጣ ጥናት ታድያ ከሦስት እና አራት ሺህ ዓመታት በፊት በዮርዳኖስ ሸለቆ ውስጥ ትገኝ የነበረች ጥንታዊቷ የታል ኤል-ሃማን ከተማ በ1,650 ዓመተ ዓለም ከህዋ በወረደ ኃይለኛ የሜትሮይቶች ስብስብ ባደረሰው ፍንዳታ (cosmic airburst) ተመታ መጥፋቷን አመላክቷል፡፡
ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ላይ እንዳስቀመጡት ክስተቱ እ.አ.አ በ1908 ከተከሰተውና ሂሮሺማ ላይ ከተጣለው ቦምብ 1ሺህ እጥፍ የላቀ ኃይልን ከለቀቀው የቱንጉሳካ ፍንዳታም የላቀ ነው፡፡ የጥናት ቡድኑ ባመላከቱት መሰረት ጥንት ከተማዋ ትገኝበት በነበረበት ቦታ ላይ 1.5 ሜትር የሚወፍር የካርበን እና አሽ ድብልቅ የሆነ አጥፊ ሽፋን ለብሶ የተገኘ ሲሆን ሽፋኑ ምናልባትም ከታሪኩ መነሻ ወቅት ጋር ሊመሳሰል እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጠው ታሪክ ላይ የሚጠቀሱት ነገሮች የሜትሮይቶች ስብስብ ምደር ላይ ሲወርድ ጋር ከሚታየው ጋር የሚመሳሰሉ ሆነው ቢገኙም የጠፋችው ከተማ ግን በመፅሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ላይ የተቀሰችው የሶዶም ከተማ መሆኗን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳላገኙ ተመራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የታል ኤል-ሀማም በዚህ መልኩ መጥፋት ኋላ ላይ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ለሰፈረው ታሪክ መነሻ ሊሆን ይችላል ሲሉ ጥጣሬያቸውን ይገልፃሉ፡፡ 




© ስፑትኒክ   













Short info

× Chat