askwala.com - የጤና ሙያ የብቃት ምዘና ከተፈተኑት ከ7 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ፈተናውን አላለፉም
Header







የጤና ሙያ የብቃት ምዘና ከተፈተኑት ከ7 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ፈተናውን አላለፉም


የጤና ሚኒስቴር ለጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ለመስጠት ወደ 15 ሺህ የሚሆኑ አዳዲስ ተማሪዎችን መመዝገቡንና የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ፣ እንዲሁም ከተመዘገቡት ውስጥ ለምዘና የቀረቡት 7 ሺህ 8 መቶ ብቻ መሆናቸውን ሰምተናል።
በጤና ሚኒስቴር የጤና በለሙያዎች ብቃት ምዘናና ሙያ ፈቃድ ረዳት አስተባባሪው አቶ ፈቃዴ ከበደ፣ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን የጤና ባለሙያ እንዲሆኑ የሚያድስላቸውን ህጋዊ ፈቃድ ለመስጠት ከ15 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደተመዘገቡ ነግረውናል።
ነገር ግን የብቃት ምዘናውን ለመውስድ ፈተና ላይ የተገኙት ወደ 7 ሺህ 8 መቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ብለዋል።
የብቃት ምዘና ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ ደግሞ 2 ሺህ 404ቱ ብቻ ናቸው ማለፍ የቻሉት ብለዋል።
ያላለፉት ተማሪዎች በመቶኛ ሲገለፅ ደግሞ 63 ከመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።
ፈተና ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉት ተማሪዎች ደግሞ የትምህርት ማስረጃዎቻቸው በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ህጋዊ መሆኑ የተረጋገጠውን ብቻ ናቸው ብለውናል።
የብቃት ምዘናውን እንዲወስዱ ከተመዘገቡት ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት ተማሪዎች፣በምን ምክንያት ፈተና ላይ ሊገኙ አልቻሉም በሚል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ምናልባት በትምህርት ማስረጃዎቸው ህጋዊ መሆን አለመሆን ላይ ይጠራጠራሉ ብለን እናስባለን ነው ያሉት።
ነግር ግን አሁንም ቢሆን የትምህርት ፤ማስረጃዎቸውን ህጋዊነት በመረጋገጥና የሙያ ብቃት ምዘናውን ፈተና መውሰድ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። 




© ኢትዮ FM 107.8   













Short info

× Chat