askwala.com - ቴሌግራም በለስ ቀናው
Header







ቴሌግራም በለስ ቀናው


ባሳለፍነው ሰኞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፌስቡክና ሌሎች የኩባንያው መተግበሪያዎች መቋረጥን ተከትሎ ሰባ ሚሊዮን አዲስ ተጠቃሚዎች ማግኘቱን ቴሌግራም አስታወቀ፡፡
የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያው መስራች ፓቬል ዱሮቭ "ስደተኞች" ሲል ለጠራቸው አዲሶቹ ተጠቃሚዎች "እንኳን በደህና መጣችሁ" ሲል መልዕክት ማስፈሩን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡
የፌስቡክና ሌሎች የኩባንያው መተግበሪያዎች ለስድስት ሰዓት ያህል ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ ከቴሌግራም ዕለታዊ አዲስ ተጠቃሚዎች በእጅጉ የላቀ የተጠቃሚዎች ቁጥር በዕለቱ ተመዝግቧል፡፡
በጥቂት የማሕበራዊ ትስስር እና የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች ላይ ብቻ እምነትን መጣል እንደማያስፈልግ የሰኞው ክስተት ጥሩ ማሳያ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘገባው አስፍሯል፡፡ 

















Short info

× Chat