askwala.com - የተጨማሪ እሴት ታክስ /Value Added Tax (VAT)/ እና ጠቀሜታው
Header







የተጨማሪ እሴት ታክስ /Value Added Tax (VAT)/ እና ጠቀሜታው


ይህ ታክስ በፍጆታ እቃ ወይም በተጠቃሚ ወጪ ላይ የተመሰረተ ሲሆን የሚሰበሰበውም ምርት ከውጭ አገር ወደ ውስጥ ሲገባ ወይም ማንኛውም ታክሱ የሚከፈልበት ዕቃና አገልግሎት ግብይት ሲካሄድባቸው ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በባህርይው ሰፊ የሆነ፣ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል ታክስ ነው፡፡ ታክሱ ከአስመጪዎችና ጥሬ ዕቃ አምራቾች አንስቶ እስከ ቸርቻሪዎች ድረስ በሚደረጉ የማምረትና የማከፋፈል /የማሰራጨት/ ሂደቶች በሁሉም ደረጃዎች በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ ይሰበሰባል፡፡
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጠቀሜታዎች መካከል
1. ምርት ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ በሚተላለፍበት ወቅት በሚፈጠር የታክስ ተንከባላይነት ባሕሪ ቀደም ብሎ የተከፈለውን ታክስ በማቀናነስ በታክስ ላይ ታክስ የማሰብ ሁኔታ እንዳይፈጠር ያደርጋል፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ጥሬ ዕቃን ጨምሮ ለማምረቻ መሳሪያዎች፣ ለማከፋፈልና ለአስተዳደራዊ ተግባራት የተከፈለ ታክስን ጭምር ተመላሽ ያደርጋል፡፡
3. ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው መጣኔ /rate/ ዜሮ በመቶ ስለሆነና ለግብአቶች የተከፈለው ታክስም ተመላሽ የሚደረግ በመሆኑ የውጭ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲበረታታ ያደርጋል፡፡ 

















Short info

× Chat