askwala.com - በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የቻይና የበላይነት
Header







በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የቻይና የበላይነት

Image name: AI_China_Us.jpg

የአሜሪካው የመከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታጎን የቀድሞ ባልደረባ በቻይና እና አሜሪካ መካከል በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በሚደረገው ፉክክር ቻይና አሸንፋ የበላይነቱን ይዛለች ሲሉ ተናገሩ፡፡
በመሥሪያ ቤቱ የሶፍትዌር ዘርፍ በዋና ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ኒኮላስ ቼለን ከፋይናንሺያል ታይምስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቻይና በረቀቁ ቴክኖሎጂዎቿ አማካኝነት ወደ ዓለም ተፅዕኖ ፈጣሪነት ደረጃ እየገሰገሰች መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ግለሰቡ አሜሪካንን አደጋ ላይ እየጣለ ነው ባሉት በመከላከያ ኃይል ውስጥ እየታየ ያለው ዘገምተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በመቃወም በፈቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን በቆይታቸው አብራርተዋል፡፡
ኒኮላስ ቼለን "በቀጣዮቹ 15 እና 20 ዓመታት ከቻይና ጋር የምንፎካከርበት ምንም አይነት እድል አይኖረንም፡፡ በእኔ አስተያየት አሁን ጉዳዩ አልቆለታል፡፡" ሲሉ ሀሳባቸውን ያጋራሉ፡፡
ለአሜሪካ ሽንፈት በዘገምተኛ ሂደት እየተጓዘ ነው ያሉት የፈጠራ ስራ እና ጉግልን የመሳሰሉ ግዙፍ ኩባንያዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ከመንግስት ጋር ለመስራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በምክንያትነት አስቀምጠዋል፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ የሥነ-ምግባር መርሆች ላይ እየተደረገ ያለው መጠነ ሰፊ ክርክርም ሌላኛው ጎታች ምክንያት ነው ሲሉ ጠቅሰውታል፡፡ 

















Short info

× Chat