askwala.com - አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመንገድ ደህንነት
Header







አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመንገድ ደህንነት

Image name: technology.jpg

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘላቂ የልማት ግቦች በመንገድ ደህንነት ዙሪያ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገለፀ፡፡
ድርጅቱ በዘላቂ የልማት ግቦቹ በዓለም ዙሪያ ያለውን ዓመታዊ ከመንገድ ጋር ተያያዥ ሞት እንደ አውሮፓውያኑ በ2030 በግማሽ ለመቀነስና ለሁሉም ተደራሽ የሆነና ደህንነቱ የተጠበቀ የመጓጓዣ አገልግሎት እውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡
ግቡን በተለይም በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ሀገራት ለማሳካት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመንገድ ደህንነት" በተባለው አዲስ እንቅስቃሴ ተመላክቷል፡፡
እንቅስቃሴው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመንገድ ደህንነት ልዩ ተልዕኮ እና በዓለም አቀፉ የቴሌኮምዩኒኬሽን ሕብረት አማካኝነት መጀመሩን ከመንግስታቱ ድርጅት የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በመንገድ ላይ የሚደርሱ የአደጋ መረጃዎችን በተሻለ መልኩ ለመሰብሰብ እና ለመተንተን፣ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ጥራት ለማሻሻል፣ ለአደጋዎች የሚሰጥ ምላሽን ብቃት እና ቅልጥፍና ለመጨመር እንደሚያገልግል በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በዓለም ዙሪያ በየዓመቱ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከመንገድ የትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ ይሞታሉ፡፡ 

















Short info

× Chat