ባሳለፍነው ሐምሌ አፕል የቺፕ እጥረቱ በማክ እና አይፓድ እንዲሁም አይፎን ምርቶቹ ላይ ተፅዕንዖ ስለሚያሳድር የገቢ እድገቱም በዚያው ልክ ሊጎዳበት እንደሚችል ትንበያ አስቀምጦ ነበር፡፡ ታድያ የትናንትናውን ዜና ተከትሎ የአፕል አክሲዮኖች የግብይት ዋጋ በ1.2 በመቶ ሲወርድ የቴክሳስ ኢንስትሩመንትስም እንዲሁ በ1 በመቶ ቀንሷል፡፡
አለም አቀፉ የቺፕ እጥረት ከመኪና አንስቶ እስከ ኤሌክትሮኒክስ እቃ አምራች ኩባንያዎች ድረስ ከፍተኛ ተፅእንዖን እያሳደረ ይገኛል፡፡ በዚህም እንደ አፕል ሁሉ በርካታ የመኪና አምራቾችም የመኪና ምርቶቻቸውን ገታ ለማድረግ ተገደዋል፡፡
አፕል ከቺፕ አቅራቢዎች ጋር በገባው የረጅም ጊዜ ውል እና ባለው ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ምክንያት ከሌሎች በተሻለ እጥረቱን ተቋቁሞ እስካሁን መዝለቁን ተከትሎ የኢንዱስትሪው ተንታኞች መስከረም ላይ ይፋ የተደረጉት ባለ 5ጂዎቹ የአይፎን 13 ስልኮች በስፋት እንደሚሸጡ ትንበያቸውን ሲያስቀምጡ ቆይተዋል፡፡ አሁን ላይ ግን የዚህ ዜና መሰማቱን ተከትሎ በገዢዎች ዘንድ ምርቱን ለመግዛት ከፍተኛ ጥድፊያ ሊፈጠር እንደሚችል ተገልጿል፡፡
© ሮይተርስ