askwala.com - የሮቦቶች የመከላከያ አባልነት በሲንጋፖር
Header







የሮቦቶች የመከላከያ አባልነት በሲንጋፖር

Image name: ghost robotics.png

የሲንጋፖር የመከላከያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተቋም ሮቦቶችን በደህንነት፣ መከላከያ እና ሰብዓዊ ተግባራት ውስጥ ተሳታፊ ለማድረግ ያለመ ስምምነት ጎስት ሮቦቲክስ ከተባለ ተቋም ጋር ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ ሮቦቶችን በደህንነት፣ መከላከያ እና ሰብዓዊ ተግባራት ውስጥ መጠቀም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ከመለየት እንደሚጀምር ዜድ.ዲኔት ዘግቧል፡፡ በተጨማሪም ለተጠቀሱት ዘርፎች የሚውሉ ተንቀሳቃሸ የሮቦት ሥርዓቶችን እና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎቸን ማበልፀግ እና መሞከር የስምምነቱ አንድ አካል ነው፡፡
ሮቦቶቹ በየትኛውም ሁኔታ እና ቦታ የተጣለባቸውን ኃላፊነት የመወጣት ብቃት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡
መቀመጫውን በአሜሪካ ፊላዴልፊያ ያደረገው ጎስት ሮቦቲክስ ለወታደራዊ እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሮቦቶችን በማበልፀግ የሚታወቅ ኩባንያ ነው፡፡ 

















Short info

× Chat