1. ሚስጢራዊ የይለፍ-ቃልዎን ደህንነት ያረጋግጡ
• ለፌስቡክ የሚጠቀሙበትን የይለፍ-ቃል በፍጹም ለሌላ የኦንላይን አካውንት አይጠቀሙ፤
• የይለፍ-ቃልዎን በፍፁም ለሌላ ሰው አያጋሩ፤
• የይለፍ-ቃልዎ ጠንካራና ለመገመት አዳጋች ሊሆን ይገባል፤ ስምዎን ወይም የተለመዱ ቃላትን በሚስጢራዊ የይለፍ-ቃልዎ ውስጥ አያካቱ፤
• ጠንካራ የይለፍ-ቃል እንዴት መፍጠር እንደሚችሉ ይማሩ /# creating a strong password/፤
2. ወደ ግል አካውንቶ ለመግባት /login/ የሚረዱ መረጃዎችን አያጋሩ
• አጠቂዎች/ጠላፊዎች አሳሳች ፌስቡክ የሚመስሉ ገጾችን በመፍጠር በኢ-ሜይል አድራሻዎ እና የይለፍ-ቃልዎ እንዲገቡ ሊጠይቋችሁ ይችላሉ፤
• ሁልጊዜም የይለፍ-ቃልዎን ከመጻፍዎ በፊት የድር-ገጹን ዩአርኤል /URL/ ትክክለኝነት ያረጋግጡ፤ አጠራጣሪ ነገር ካጋጠመዎት www.facebook.com በማፈላለጊያ መረቡ ላይ በመጻፍ ትክክለኛው የፌስቡክ አድራሻ መሆኑን ያረጋግጡ፤
• ስለአካውንቶ ምስጢራዊ ወይም ጥብቅ መረጃ የያዙ ኢ-ሜይሎችን በፍጹም በፌስቡክ ወደ ሌሎች ሰዎች አይላኩ፤
• ፊሺንግን /Phishing/ እንዴት እንደሚያስወግዱ ይማሩ /# avoiding phishing/
3. የሚጠቀሙበትን መሣሪያ /device/ ለሌሎች ሰዎች የሚያጋሩ ከሆነ አካውንቶን ዘግተው መውጣቶን ያረጋግጡ፤
• አካውንቶን ሳይዘጉ የግል መሣሪያዎን ለሌሎች ሰዎች ካዋሱ ካሉበት ርቀት ላይ ሆነው ዘግተው መውጣት ይችላሉ /# log out remotely/፤
4. ከማያውቁት ሰው ለሚቀርብ የጓደኝነት ጥያቄ ምላሽ አይስጡ
• ጠላፊዎች /Scammers/ ሰዎችን ለማጥመድና ጓደኛ ለማድረግ የሐሰት አካውንት ሊፈጥሩ ይችላሉ፤
• የጠላፊዎች ጓደኛ ከሆኑ የየዕለት የፌስቡክ እንቅስቃሴዎትን ሊከታተሉ፣ የራሳቸው መልዕክቶች በእርሶ ገጽ ላይ ሊያጋሩ እና አጥፊ ቫይረሶችን በመልዕክት መቀበያ ሳጥኖች ሊሊኩባችሁ ይችላሉ፤
5. አጥፊ ሶፍትዌሮችን ይከታተሉ
• አጥፊ ሶፍትዌሮች ኮምፒውተርዎን፣ ሰርቨሮን ወይም የኮምፒውተር ኔትወርኮን ሊበክሉ ይችላሉ፤
• የተጠቃ ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ባህሪ ይማሩ /#Learn the signs of an infected computer /፣ እንዴት አጥፊ ሶፍትዌሮችን እንደሚያስወግዱም ይወቁ፤
• በየጊዜው የገጽ ማፈላለጊያዎን ያዘምኑ፣ አጠራጣሪ መተግበሪያዎችን ወይም ማስታወቂያ የያዙ /# browser add-ons/ ጥያቄዎችን ያስወግዱ፤
6. በፍጹም አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን /links/ አይክፈቱ
• በፌስቡክ (ለምሳሌ በፌስቡክ ገጾች ላይ የተጋሩ ማስፈንጠሪያዎች/ ወይም በኢ-ሜይል የተላኩ ማስፈንጠሪያዎች አይክፈቱ፤
• ፌስቡክ በፍጹም በኢ-ሜይል አካውንቶ የይለፍ ቃልዎን እንዲያስገቡ እንደማይጠይቆ ያስታውሱ፤
• ፌስቡክ ላይ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያ ካጋጠመዎት ሪፖርት ያድረጉ /#report it/;
7. ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀሙ
• ከማይታወቁ አድራሻዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት እንዲደርስዎ ያድርጉ፤ /#get alerts about unrecognized logins/ ተጨማሪ የማንነት ማረጋገጫ ሥርዓት /#set up two-factor authentication/ ይጠቀሙ፤
• ወደፌስቡክ በኮምፒውተር ከገቡ፣ የደህንነት መጠበቂያ መዋቅር /#Security Checkup/ ከደህንነት መጠበቂያ መዋቅሩ ውስጥ መጠቀም ይችላሉ፡፡