ሥርዓቱ ፈንደስ ተብሎ የሚታወቀውን ለዓይን ምርመራ የሚውል የፎቶግራፍ ዘዴ ሬቲና ላይ በሚከሰቱ በሽታዎች ከሰለጠነ የዲፕ ለርኒንግ ሥርዓት ጋር በማጣመር ለውጤት መብቃቱን ዜድ.ዲኔት ዘግቧል፡፡
ኬር የሚል መጠሪያ የተሰጠው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በብዛት ሬቲና ላይ የሚከሰቱ 14 አይነት በሽታዎችን የመለየት አቅም እንዳለው ተጠቅሷል፡፡
የዲፕ ለርኒንግ ሥርዓቱን ለማሰልጠን ከአፍሪካ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የተውጣጡ ከ ሁለት መቶ ሺ በላይ የዓይን የውስጠኛው ክፍል ፎቶግራፎች ጥቅም ላይ መዋላቸው ተገልጿል፡፡
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቱ የተደረጉ ምርመራዎችን በሐኪም ከተደረጉት በማነጻጸር የተገኘው ውጤት እጅግ አመርቂ መሆኑን የምርምር አባላቱ አብራርተዋል፡፡