ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገው ሽልማት የዘንድሮ አሸናፊ በአሜሪካው ድዩክ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዩተር ሳይንቲስት የሆኑት እንስት በዘርፉ ለአስራ አምስት ዓመታት ሲሰሩ መቆየታቸውን የሽልማት ተቋሙ መረጃ አመላክቷል፡፡
ማሕበራዊ ኃላፊነት የሚሰማው እና በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ቀጥተኛ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ትግበራ ዙሪያ በመስራታቸው ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው ተገልጿል፡፡
ሳይንቲስቷ ሰዎች በቀላሉ የሚረዷቸውና እራሳቸውን መግለፅ የሚችሉ የትንበያ መላምቶችን interpretable machine learning በተባለ ስልት በማበልፀግ ለዘርፈ ብዙ ማሕበራዊ አገልግሎቶች እንዳዋሉ ተብራርቷል፡፡
በዚህም በፍትሕ ሥርዓት ፣በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና በጤናው ዘርፍ የተመራማሪዋ ስራዎች በተግባር ውለው ለተግዳሮቶች መፍትሔ መሆን ችለዋል፡፡
ሽልማቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሰው ልጅ የተሻለ ጥቅም እንዲውል ስኩዊረል ኤ.አይ በተባለ የበይነ መረብ የትምህርት ተቋም የገንዘብ ድጋፍ በAAAI - Association for the Advancement of Artificial Intelligence በየዓመቱ የሚበረከት መሆኑ ታውቋል፡፡