ስሞል ስማርት ሰሌክሽን የተባለው በኩባንያው ስራ ላይ የዋለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተ ቀመር የደምበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ የግብይት ጥቆማን ያቀርባል፡፡
የደምበኞቹን ዘጠና በመቶ ጥያቄዎች የሚያስተናግድ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አቅም ያነገበ ቻትቦት (ውይይት መለዋወጫ ሮቦት) ሌላኛው በኩባንያው ስራ ላይ ውሎ ውጤታማ የሆነ የዘርፉ አበርክቶ ነው፡፡
ኩባንያው ከሁለት መቶ በላይ የሆኑ ሮቦቶችን በመጠቀም በቀን አንድ ሚሊዮን ጭነቶችን ዝግጁ በማድረግ የመጋዘን እንቅስቃሴውንም ያቀላጥፋል፡፡
አሊባባ በ2017 (እ.ኤ.አ) አስራ አምስት ቢሊዮን ዶላር በጀት በመመደብ ሰባት የጥናት እና ምርምር ተቋማት አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ማሽን ለርኒንግ፣ ናቹራል ላንጉዬጅ ፕሮሰሲንግ እና የኔትዎርክ ደህንነት ደግሞ ማዕከላቱ ምርምር ከሚያደርጉባቸው መካከል ናቸው ሲል አናሊቲክስ ኢንሳይት ዘግቧል፡፡