askwala.com - አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመድኃኒት ግኝት
Header







አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለመድኃኒት ግኝት


በለንደን በሚገኘው የካንሰር ምርምር ኢንስቲትዩት የሚገኙ ተመራማሪዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ለሕጻናት የጭንቅላት ካንሰር ሕክምና የሚውል የመድኃኒት ጥምረት መፍጠራቸው ተገለጸ፡፡
Diffuse Intrinsic Pontine Glioma (DIPG) ተብሎ ለሚጠራው ሕጻናት ላይ ለሚከሰት አደገኛ የጭንቅላት ካንሰር አይነት ቫንዴታኒብ እና ኤቨሮለመስ የተባሉ ሁለት መድኃኒቶችን በማጣመር ውጤት መገኘቱን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡
የሁለቱ መድኃኒት ጥምረት በአይጦች ላይ ተሞክሮ ከመደበኛው የሕክምና መንገድ በተሻለ ባሳየው ውጤት አራት ሕጻናት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ለማድረግ መቻሉ ተነግሯል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የሕጻናት የጭንቅላት ዕጢ ፕሮፌሰር የሆኑት ክሪስ ጆንስ ግኝቱን አስመልክቶ እንዳሉት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ጥቆማ አማካኝነት ሁለቱን ነባር መድኃኒቶች በማጣመር የተሻለ ውጤት መገኘቱን አብራርተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ DIPGን ለመሳሰሉ ካንሰሮች መድኃኒት ፍለጋ ለሰው ልጆች ያልተገለፀውን በመፍታት ረገድ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉልህ ሚና እንዳለው የምርምር ቡድናቸው ግኝት አመላካች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ 

















Short info

× Chat