askwala.com - \"ሜታ\" አዲሱ የፌስቡክ ስያሜ
Header







"ሜታ" አዲሱ የፌስቡክ ስያሜ

Image name: Meta.jpg

አዲስ ገጽታ እና የስያሜ ለውጥ እንደሚያደርግ ሲነገርለት የቆየው ፌስቡክ አዲሱን ስያሜ እና ዓርማውን አስተዋወቀ፡፡
ከስያሜ እና የዓርማ ለውጡ ጀርባ ኩባንያው ከማሕበራዊ ትስስር ተቋምነት ባሻገር ምናባዊ እውነታን (Virtual Reality) ያካተተ ተቋም የመሆን ራዕይ ማንገቡን ቢ.ቢ.ሲ አስነብቧል፡፡
ሜታ በሚል በአዲስ ስያሜ እና ዓርማ የመጣው ኩባንያ እንደ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ሌሎችም ነባር የኩባንያውን መተግበሪያዎች እንደሚያስተዳድር ተገልጿል፡፡
ኩባንያው አድማሱን በማስፋት ሜታቨርስ ወደሚባለው በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ እና ሰዎች የምናባዊ እውነታ መሣሪያዎችን (Virtual Reality Headsets) ተጠቅመው ስራ የሚሰሩበት፣ እርስ በርስ የሚገናኙበት እና ጨዋታዎችን በጋራ የሚጫወቱበት የበይነ መረብ ምናባዊ ከባቢን የመፍጠር እቅዱንም አስተዋውቋል፡፡ 

















Short info

× Chat