askwala.com - ካንሰርን በማሽን ለርኒንግ
Header







ካንሰርን በማሽን ለርኒንግ


ባለብዙ ስልተ-ቀመር ማሽን ለርኒንግን ጥቅም ላይ በማዋል የካንሰር ታማሚዎች ለሕክምናው የሚያሳዩትን ምላሽ ለማወቅ የሚረዳ ሥርዓት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡
የማሽን ለርኒንግ ስልተ-ቀመሩ በሕክምና ሂደት ጥቅም ላይ ለሚውሉ ካንሰርን ለሚዋጉ መድኃኒቶች የታማሚዎችን ምላሽ ቀድሞ ለመተንበይ ያስችላል፡፡
በዚህም በሕክምናው ዘርፍ ያሉ መጠነ ሰፊ እና ውስብስብ ዳታዎችን በመሰል ሥርዓቶች በመተንተን የሕክምና ባለሞያዎች ለእያንዳንዱ ታማሚ ምን አይነት የሕክምና ሂደት መከተል እንደሚገባቸው የሚያስገነዝብ መረጃ እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡
ሥርዓቱን የጂዮርጂያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የኦቫሪያን ካንሰር ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች በጋራ በመሆን እንዳበለፀጉት ሄልዝ አይ.ቲ አናሊቲክስ አስነብቧል፡፡
የምርምር ቡድኑ ሥርዓቱን ለማበልፀግ ከአሜሪካው ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ከተወሰዱ 499 ሕዋሶች የተገኘውን ዳታ በመጠቀም ለ15 የካንሰር አይነቶች የሚውል የማሽን ለርኒንግ የትንበያ ሥርዓት ማበልፀግ መቻላቸው ተመላክቷል፡፡
ሥርዓቱ በ23 የማሕፀን ካንሰር ታማሚዎች ላይ ተሞክሮ 90 በመቶ ስኬታማ ነው፡፡ 

















Short info

× Chat