askwala.com - የአልፋቤት አዲስ የመድኃኒት ግኝት እቅድ
Header







የአልፋቤት አዲስ የመድኃኒት ግኝት እቅድ


የጉግል እናት ኩባንያ የሆነው አልፋቤት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ታግዞ መድኃኒቶችን ለማግኘት የሚሰራ አይሶሞርፊክ ላብስ የተሰኘ ተቋም መሰረተ፡፡
አዲሱ ተቋም አዳዲስ መድኃኒቶችን ለማግኘት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ከሚጠቀሙ የሕክምና እና መድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ጋር በአጋርነት ለመስራት ማቀዱን ሲኔት ዘግቧል፡፡
በተቋሙ ምስረታ ማብሰሪያ ላይ ሳይንቲስቶች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የመሰሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ማዋላቸው ምርምራቸውን ከማዘመኑ ባሻገር አዳዲስ መድኃኒቶችን ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያፋጥነው ተመላክቷል፡፡
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በዘርፉ ያለውን ዳታ ከመተንተን ባለፈ በውስብስብ የሥነ-ሕይወት ጉዳዮች ዙሪያ ጠንካራ ትንበያዎችን ለማበልፀግ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡ 

















Short info

× Chat