ይህ ከዓለም የሚተካከለው እንደሌለ የተነገረለት ልዕለ ኮምፒዪተር የላቀ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ባለቤትም ጭምር ነው፡፡
ያከናውናቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ትልልቅ ጉዳዮች መሀል ለአፅናፈ ሰማይ (Universe) የ3ዲ ካርታ ዝግጅት Dark Energy Spectroscopic Instrument (DESI) ከተባለው የጠፈር ካሜራ የሚገኘውን ዳታ በመተንተን ትልቅ ግብዓት እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
ኮምፒዉተሩ በርክሌይ ላብ ተብሎ በሚጠራው የአሜሪካ ብሔራዊ የኃይል ምርምር ቤተ ሙከራ (National Energy Research Scientific Computing Center (NERSC)) ውስጥ ነዉ ስራ የጀመረዉ፡፡ ኤንቪዲያ እና ሂውለት ፓከርድ ኩባንያዎች ደግሞ ኮምፒዩተሩን ለውጤት አብቅተዉታል፡፡
ኤንቪዲያ ድረ-ገፅ ላይ በወጣው መረጃ መሠረት በአውሮፓውያኑ ወርሐ ግንቦት 2021 ዓ.ም ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡