1. #የድርጅት_ከሆነ፦ የድርጅቱ ንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የተጠቃሚው መታወቅያ ኮፒ እንዲሁም ተወካይ ከሆነ የድርጅቱ የውክልና ደብዳቤ፣ የዕቃው ዓይነት፣ የዕቃው ሞዴል ቁጥር፣
2. #የግለሰብ_ከሆነ፡- መታወቅያ ኮፒ እንዲሁም ተወካይ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ፣ የዕቃው ዓይነት፣ የዕቃው ሞዴል ቁጥር፣
3. ሁሉም የዕቃ አስመዝጋቢ የመሳሪያዎቹን አይነት በኤጅንሲዉ በአካል ይዞ መምጣት የሚቻለው ከሆነ ከዕቃዎቹ ዓይነት አንዳንድ ሳምፕል ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
#ማስታወሻ፦
• ለክልል (በጣም ርቀት ቦታ ላይ ላሉ ብቻ ተግባራዊ የሚሆን የቴሌግራም ተመዝጋቢዎች) 0911866228 ይህን ስልክ ቁጥር በመጠቀም መመዝገብ ይቻላሉ።
• በአዲስ አበባ እና በዙሪያው የሚገኙ አካላት በአካል ቀርበው ማስመዝገብ ግዴታ ያለባቸዉ ሲሆን በቴሌግራም ማስመዝገብ አይቻልም፡፡
• ከክልል የሚያስመዘግቡ አካላት ከየት ክልል እንደሆነ በአግባቡ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
#ማሳስቢያ
እነዚህን የመገናኛ እና ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ ወይም በተቋማት ውስጥ ሲጠቀም ያየ ማንኛዉም አካል ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጅንሲ በነጻ ስልክ ቁጥር 933 ወይም 0900672342፣ 0113851193፣ 0904049625 እና 0114701321 ማሳወቅ ይጠበቅበታል።
ላይ ከተጠቀሱ መሣሪያዎች ውስጥ በእጁ የሚገኝ ማንኛውም አካል በአካል በኢመደኤ /INSA/ ዋናው መ/ቤት (ቦሌ ወሎ ሰፈር) ከሰኞ ህዳር 13 ቀን፣ 2014 ዓ.ም ጀምሮ መሳሪያውን በመያዝ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
አካባቢያችንን ነቅተን እንጠብቅ!!
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ