ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ #Wordtune_Read የተሰኘ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ሰዎች ረዣዥም እና ውስብስብ ጽሁፎችን በተሻለ ፍጥነት አንብበው እንዲረዱ የሚያስችል መሆኑን ኤ.አይ ኒውስ አስነብቧል፡፡
ረዘም ያሉ ጽሁፎችን የያዙ ድረ-ገጾችን አድራሻ ለመተግበሪያው በመስጠት ወይም የፒ.ዲ.ኤፍ ሰነዶችን በመጫን አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡
መተግበሪያው የሥራ ሪፖርቶችን፣ ረዥም ዜናዎች እና መሰል ጽሁፎችን እንዲሁም ትምህርት-ነክ ጽሁፎችን ጨምሮ የሌሎች ንባቦችን አንኳር ጉዳዮች ለይቶ በማሳጠር ሰዎች ሳይሰላቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያነቡትን ጉዳይ ፍሬ ነገር መረዳት እንዲችሉ ያግዛል ተብሎለታል፡፡
መሰል መተግበሪያዎች በማሽን ለርኒንግ በተለይም በሪኢንፎርስመንት ማሽን ለርኒንግ አማካኝነት ይበለፅጋሉ፡፡ በሂደት ከተጠቃሚዎች በሚሰጣቸው የአዎንታ እና የአሉታ ግብረ-መልስ በመነሳት እራሳቸውን እያሻሻሉ የሚሄዱ ስልተ-ቀመሮች በመሰል መተግበሪያዎች አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡
እርስዎም ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን አገልግሎቱን እንዲሞክሩ ጋብዘንዎታል