እነዚህ ሃሰተኛ መረጃዎችም በተለያዩ የዲጂታል የሚዲያ አማራጮች በስፋት ሲሰራጩ ይስተዋላል። በመሆኑም እነዚህን ሃሰተኛ መረጃዎች ለመለየት ከዚህ በታች የተቀመጡ አማራጮችን መጠቀም ይቻላል።
1. #ምንጩን_በአንክሮ_መመርመር (examine the source)
የመረጃው ምንጭ ማነው? ዌብሳይቱ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ገፁ የሚታወቅ እና የሚታመን ነው? ትክክለኛው የሚዲያው አድራሻ ነው?
2. #ርዕሱና_ይዘቱን_ማመሳከር (headline vs content)
ለመረጃው የተሰጠው ርዕስና በመረጃው የተካተተው ይዘት ተመሳሳይና ተስማሚ ነው? ለመረጃው የተሰጠው ር ዕስ ስሜት ኮርኳሪና የጥድፊያ ስሜትን እንዲያነሳሳ የታሰበ ነው? ርዕስ አሰጣጡ ሆን ተብሎ የሰዎችን ትኩረትና እይታ ለመሳብ የታቀደ ነው? ሰዎች መረጃውን በፍጥነት እንዲያጋሩት የታሰበ ነው?
3. #ከሌሎች_ምንጮች_ጋር_ማመሳከር (triangulation)
ስለጉዳዩ ሌሎች ታዋቂና ታማኝ ምንጮች ምን እያሉ ነው? ስለ አጀንዳው/ጉዳዩ ሌሎች ቦታዎች ላይ የተባለ ነገር አለ?
4. #በመረጃው_የተጠቀሱ_ዳታዎችን_መመርመር (check the facts)
በመረጃው ውስጥ የተገለፁና የተዘርዘሩ ዳታዎች፣ ቁጥሮች፣ ቀኖች ትክክለኛ ናቸው? መረጃው አሁናዊ ነው? ለማስረጃ የተቀመጡ ማጣቀሻዎች ትክክለኛ እና ያሉ ናቸው? የተቀመጡ ማስፈንጠሪያ ሊንኮች ትክክለኛ ናቸው?
5. #ምስሎችን_በምልሰት_መመርመር (Image reverse search)
በመረጃው ላይ የተሰራጩ ምስሎች ከዚህ በፊት ሌሎች መረጃዎች ጋር የተሰራጨ ነው? ምስሉ ሌላ አካባቢ እና በሌላ ጊዜ የተከሰተ ድርጊት ማሳያ ነው? ምስሉ መጀመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው መቼ ነው የሚለው እንደ ጎግል ኢሜጅ (google image) እንደ image reverse search ቱሎችን በመጠቀም መመርመር ያስፈልጋል።
6. #እውነትን_አፈላላጊ/አረጋጋጭ ድረ-ገፆችን መጠቀም (fact checking websites)
በተለይ አለም አቀፍ ዜናዎችና መረጃዎችን እወነትነት ለማረጋገጥ ታዋቂ የfact checking ደረገፆችን መጠቀም ያስፈልጋል።