የንዑስ ፕላኔቶቹን ምንነት ኬፕለር ከተባለው የተቋሙ ቴሌስኮፕ የተሰበሰበ መረጃን በሥርዓቱ አማካኝነት በመተንተን ለማረጋገጥ መቻሉን ቪ.ኦ.ኤ ዘግቧል፡፡
የንዑስ ፕላኔቶቹን መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ቴሌስኮፑ በሺዎች ከሚቆጠሩ ከዋክብት የሚሰበስበውን መረጃ ያለስህተት ለማረጋገጥ ግኝቱ የተሻለ አማራጭ መሆኑ በዘገባው ተብራርቷል፡፡
ከቴሌስኮፑ የሚሰበሰቡ ግዙፍ መረጃዎችን በሰዎች አማካኝነት ለመተንተን እና ለማረጋገጥ ረዥም ጊዜ እና ድካም የሚጠይቅ በመሆኑ የማሽን ለርኒንግ ሥርዓቱ በዘርፉ ለተሰማሩ ተመራማሪዎች እጅግ አስፈላጊ የሆነ እገዛን ይዞ መምጣቱ ተጠቁሟል፡፡
ንዑስ ፕላኔቶች (Exoplanets) ከሥርዓተ ፀሐይ ውጪ የሆኑና በከዋክብት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ፕላኔቶች ናቸው፡፡ ለሰው ልጅ ኑሮ ከምድር ባሻገር ምቹ ስፍራ የመፈለግ ስራው በነዚህ ፕላኔቶች ላይ የሚደረገው ምርምር አካል ነው፡፡