የስለላ ድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሪቻርድ ሙር ሁለቱ ሀገራት የስለላ እና የቀጠናውን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ቅርጽ መለወጥ የሚችሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ለማበልፀግ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ እያወጡ መሆናቸውን ገልፀዋል ሲል አልጀዚራ አስነብቧል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለጻ ተቀናቃኞቻችን ያሉዋቸው ሁለቱ ሀገራት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኳንተም ኮምፒዩቲንግ እና በሰው ሰራሽ ሥነ-ሕይወት (synthetic biology) ላይ ከፍተኛ ተነሳሽነት እና ሃብት በመመደብ ልህቀት ላይ ለመድረስ እየሰሩ ይገኛል፡፡