askwala.com - በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተገኘው አዲስ ሒሳባዊ ንድፍ
Header







በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተገኘው አዲስ ሒሳባዊ ንድፍ

Image name: A new mathematical theorem developed by AI.jpg

“ሰዎች ሳያዩ ያለፏቸው ሒሳባዊ ግንኙነቶች በማሽን ለርኒንግ ለመጀመሪያ ጊዜ መታየት ቻሉ፡፡” ይላል ታዋቂው ኔቸር የሳይንስ ጆርናል በዘገባው፡፡
ግኝቱ ይፋ የሆነው የጉግል እህት ኩባንያ ዲፕማይንድ እና የሒሳብ ሊቃውንት ባደረጉት ምርምር ነው፡፡ በምርምሩ ኖት (knot) እና ሲሚትሪ (symmetry) በተባሉ የሒሳብ ፅንሰ ሀሳቦች ዙሪያ ያሉ ስሌቶችን ለመፍታት ማሽን ለርኒንግ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
በውጤቱም በቀጣይ በመደበኛ የሒሳብ ስልቶች ምርምር ሊደረግበት የሚችል አዲስ ንድፍ መገኘቱ ታውቋል፡፡
በምርምሩ የተሳተፉት ማርክ ላከንባይ የተባሉ የኦክሰፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር እንዳሉት የሒሳብ ስሌቶቹን ለመፍታት የሰውን እውቀት እና ግንዛቤ ፈር በማስያዝ ረገድ ማሽን ለርኒንግ አስገራሚ ሚና ነበረው ሲሉ ስለሁኔታው አብራርተዋል፡፡ 

















Short info

× Chat