ቴክኖሎጂው ምን ያህል ለዕለታዊ ሕይወታችን ቅርብ እንደሆነ ለማሳየት በስማርት ስልኮቻችን በቀላሉ ተጭነው የተለያየ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የቴክኖሎጂው ውጤት ከሆኑ መተግበሪያዎች መካከል አናሊቲክስ ስቴፕስን ዋቢ አድርገን ሁለቱን እናስተዋውቃችሁ፡፡
#ELSA_Speak
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎትን በተለይም የንግግር ቅላጼን ለማሻሻል ፍላጎቱ ላላቸው የቀረበ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የሚታገዝ መተግበሪያ ነው፡፡
የሚቀርቡልንን ዓረፍተ ነገሮች በማንበብ በመተግበሪያው የድምፅ መቀበያ እንቀዳለን፡፡ ንግግራችንን በማዳመጥ ያለንበትን ደረጃ ጨምሮ ልናሻሽላቸው የሚገቡ የቃላት አጠራሮችን መተግበሪያው ወዲያውኑ ያሳውቀናል፡፡
#Socratic
ሶክራቲክ የኮምፒዩተር ቪዥን ቴክኖሎጂን አካቶ ለሁለተኛ ደረጃ እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቀረበ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ነው፡፡ ተማሪዎች ከተሰጣቸው የቤት ስራ የከበዳቸውን ጥያቄ በመተግበሪያው አማካኝነት ፎቶ በማንሳት ይልካሉ፡፡ ለጥያቄያቸው የተብራራ መልስም ከመተግበሪያው ይቀርብላቸዋል፡፡
እርስዎም መተግበሪያዎቹን በስልክዎ ጭነው በመሞከር የቴክኖሎጂው ተቋዳሽ እንዲሆኑ እንመክራለን፡፡