ሥርዓቱ የወንጀሉን ሁኔታ የቃላት መግለጫ መሠረት በማድረግ በዘጠና ሰባት በመቶ የትክክለኛነት ንጻሬ ክስ መመስረት እንደሚችል ኮሪያን ታይምስ አስነብቧል፡፡
ሥርዓቱን ለማበልፀግ ከአውሮፓውያኑ 2015 እስክ 2020 ባለው ጊዜ የነበሩ አስራ ሰባት ሺህ የክስ ጉዳዮች ለማሽን ስልጠና መዋላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
በዚህም መሠረት በቻይናዋ ሻንጋይ ከተማ በብዛት የሚከሰቱ ተብለው ለተጠቀሱ የወንጀል እንቅስቃሴ ተሳታፊዎች ክስ መስራቹ ይኸው ሥርዓት ነው፡፡ እንደ የዱቤ ካርድ ማጭበርበር፣ ሕገ-ወጥ የቁማር እንቅስቃሴዎች፣ በአደገኛ ሁኔታ ማሽከርከር፣ ስርቆት እና ተያያዥ ወንጀሎች ደግሞ የከተማዋ አንድ አካል ናቸው፡፡
በቻይና መንግሥታዊ መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት ብቃትን ለማሻሻል፣ ሙስናን ለመከላከል እና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የተለያዩ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተገበረች መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡