ለአብነትም በጤናው ዘርፍ ዳያቤቲክ ሬቲኖፓቲ የተባለውን የዓይነስውርነት መንስኤ ለመከላከል ኔትራ ኤ.አይ የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡
እንደ ኤም.ኤስ.ኤን ድረ-ገፅ ሀተታ ሶፍትዌሩ ዲፕ ለርኒንግ የተባለውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ይጠቀማል፡፡ በውጤቱም ሬቲና ተብሎ የሚታወቀውን የዓይን ክፍል ጤናማነት ከዶክተሮች እኩል የማረጋገጥ ብቃት አለው፡፡
በቀላሉ መታከም የሚችለው ይህ ሕመም በዓይን ሐኪሞች እጥረት ምክንያት በተለይም በገጠራማዋ ሕንድ ብዙዎችን ለዓይነስውርነት ይዳርጋል፡፡
በሌላ በኩል በተለያየ ምክንያት የእይታ መጠናቸው ደካማ ለሆኑ ሰዎች ሲይንግ ኤ.አይ የተባለ የምርምር ስራውን ማይክሮሶፍት አቅርቧል፡፡ የኮምፒዩተር እይታን፣ ምስል እና ንግግርን በመገንዘብ እንዲሁም ማሽን ለርኒግን በመጠቀም ሰዎች አካባቢያቸውን እንዲረዱ፣ ፅሁፎችን እንዲያነቡ እና የገንዘብ ኖቶችን እንዲለዩ አስችሏል፡፡
ሕንድ የትምህርት ዘርፉንም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተቃኘ ለማድረግ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር እየሰራች ነው፡፡ የዘጠነኛ እና የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በአማራጭነት እንዲማሩ በትምህርት ስርዓቷ አካታለች፡፡ በዚህም በሁለት መቶ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ አስራ አምስት ሺህ ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡