askwala.com - ግብርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት
Header







ግብርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት


የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (FAO) እንደሚለው ዓለም አቀፉ የምግብ እና የእርሻ ዘርፍ ከፊቱ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል፡፡ በአውሮፓውያኑ 2050 የዓለማችን የሕዝብ ቁጥር ለአስር ቢሊዮን ጥቂት የቀረው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን ያህል የሕዝብ ቁጥር ለመመገብ ደግሞ የምግብ ምርትን 70 በመቶ መጨመር እንደሚገባ ድርጅቱ ያሳስባል፡፡
ለዚህ ግዙፍ ተግዳሮት መፍትሔ ሆነው ከመጡ የዘመን ነፀብራቆች መካከል ደግሞ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎች ይጠቀሳሉ፡፡
22 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ሕዝብ 10 በመቶ ብቻ ለእርሻ ተስማሚ በሆነ መሬት እየመገበች የምትገኘው ቻይና ለዚህ የቴክኖሎጂ ኃያልነት ሕያው ምስክር ናት፡፡
በፋኦ መረጃ መሠረት ቻይና ይህን መሰል እድገት ማስመዝገብ ካስቻሏት ምክንያቶች መካከል የግብርና ዘርፉን ከጉልበት ወደ ቴክኖሎጂ ተኮር መቀየር መቻሏ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፡-
⭕️ በሮቦቶች አማካኝነት ሰፋፊ የእርሻ መሬት ላይ ያሉ ምርቶችን ለመሰብሰብ፣
⭕️ በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት የአፈር እና የአዝዕርት ጤናማነትን ለመከታተል፣
⭕️ አረም እና ተባዮችን በአነፍናፊ (sensor) አማካኝነት በመለየት እና ድሮኖችን በመጠቀም አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ፣
⭕️ ለአዝዕርቱ ተስማሚ የአየር ሁኔታን ለመተንበይ፣
⭕️ ጥልቅ የሆነ የገበያ ትንተና በመስራት ትርፋማነትን ለማረጋገጥ እና ለመሰል ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ይውላል፡፡ 

















Short info

× Chat