ለምሳሌ ትልቅ ሽልማት እንዳሸነፉ የሚገልፁ መልእክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ይህም የሚከሰተው አንድ አጥቂ የታመነ አካል በመምሰል የተጠቂውን ኢ-ሜይል ፈጣን መልእክት ወይም የጽሑፍ መልእክት እንዲከፍት በማድረግ የሚፈጸሙ ናቸው።
ቀጥሎም በከፈተው ኢ-ሜይል ላይ አጥፊ ተልእኮ ባዘሉ አገናኞች /links/አማካኝነት ወደ ሚፈልጉት አደገኛ ገጽ እንዲገቡ በማድረግ ጠቃሚ ወይም ሚስጥራዊ መረጃ ለአደጋ ይጋለጣል።
የፊሺንግ ጥቃቶችን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው የጥንቃቄ ርምጃዎች
• ኢንተርኔት ከፍተን ያለፍቃዳችን ብቅ እያሉ እንድንጭናቸዉ የሚጠይቁ ማስታውቂያዎች ዉስጥ በመግባት ሚስጥራዊ መረጃዎችን ከማስገባት መቆጠብ፤
• የግል እና ሚስጥራዊ መረጃዎን እንዲሁም የገንዘብ ነክ መረጃን በበይነመረብ ላይ በጭራሽ አለማጋራት ፤
• የመረጃዎቻችንን መጠባበቂያ (backup) መያዝ መረጃዉ ቢጠፋ ወይም ቢውደም መረጃዎቹን መተካት የሚያስችል ምትክ መጠባበቂያ መያዝ፤
• የሚጠቀሙትን የድረ-ገጽ ደህንነት ማረጋገጥ በመርጃ ማፈላለጊያዉ (browsers) የአድራሻ ባር ላይ (HTTPS) መኖሩን በማየት ማረጋገጥ፤
• አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፋየርዎልን (firewall) መጫን ኮምፒዉተር ላይ አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ሶፍትዌሮች እንዳይገቡ መከላከላል፤
• የባለብዙ ደረጃ የደህንነት ማረጋገጫ መጠቀም ለምሳሌ የአንድ ጊዜ የይለፍ-ቃል በኤስኤምኤስ መልእክት በኩል የሚገባ፣ physical token፣ የባዮሜትሪክ አይዲ/ID ተግራዊ ማድረግ።
• የኦንላይን ላይ መለያዎችዎን በመደበኛነት ይመልከቱ ወይም ያረጋግጡ ለምሳሌ
o የይለፍ-ቃሎችን በመደበኛነት መቀየር፣
o የእርስዎን የባንክ ሂሳብ መግለጫዎች/statements/በመደበኛነት ያረጋግጡ
• የመርጃ ማፈላለጊያዎን(web browser) ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፤
• አላስፈላጊ የሆኑ የኢሜይል መልዕክትን ማጣራት /Filter Spam/
የማይታወቁ ወይም አስፋላጊ ያልሆኑ የኢ-ሜይል መልእክቶች ወደ ግልዎ ወይም የድርጅትዎ የመልእክት ሳጥን እንዳይገቡ ማገድ፥
• ሰዋሰዋዊ ስህተቶች እና የፊደል ግድፈቶች ያሉባቸው ድረ-ገፆችን ሁልጊዜ በትኩረት ማየት እና አለመጠቀም።
* ያለዎትን ማንኛውንም ሚስጥራዊነት ያለው የግል መረጃ መስጥሮ መያዝ።