askwala.com - የሳይበር ደህንነት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሲፈተሸ
Header







የሳይበር ደህንነት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሲፈተሸ


የሳይበር ምህዳሩን ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ ለውጥ እያሳየ በሚገኘው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (የሰው ሰራሽ አስተውሎት) ቴክኖሎጂ አማካኝነት አስተማማኝ ለማድረግ ምርምሮች እየተደረጉ ይገኛል፡፡
በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት የተቋምን የዳታ መዋቅር ትንተና መሠረት አድርጎ የማያቋርጥ የስጋት ማነፍነፍ ተግባራት ማከናወን ይቻላል፡፡ የማሸን ለርኒንግ ስልተቀመሮቹ የተቋሙን የኔትዎርክ መሠረተ ልማቶች በመረዳት ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት የተጋላጭነት ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን ያስተላልፋሉ፡፡
በዩር ስቶሪ ድረ-ገፅ ትንተና መሠረት መሰል ስልተቀመሮች የተጠቃሚዎችን የዕለት ከዕለት የበይነመረብ ባሕርያት መሠረት አድርገው የስጋት ማስጠንቀቂያዎችን እና መሰል እርምጃዎችን ይወስዳሉ፡፡ ለአብነትም አንድ ግለሰብ በየዕለቱ ከሚጠቀምበት የኤልክትሮኒክስ መሣሪያ ለውጥ ቢያደርግ፣ የቦታ ለውጥ አሊያም ያልተለመዱ ወደ ድረ-ገፁ ለመግባት የሚደረጉ ሙከራዎችን በመለየት ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ፡፡
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለሳይበር ደህንነት ከላይ ከተጠቀሱት ባሻገር ገንዘብ ነክ የማጭበርበር ሙከራዎችን ለመግታት ጭምርም ይውላል፡፡
ሳይበር ሴኪዩሪቲ ቬንቸርስ የተባለው ድረ-ገፅ ባወጣው መረጃ በሳይበር ጥቃት ምክንያት የሚደርሱ ኪሳራዎች እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ከነበረበት የሦስት ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በ2025 አስር ትሪሊዮን እንደሚደርስ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡ 

















Short info

× Chat