እንዲሁም እነዚህ አገናኞች ወደ ሐሰተኛ ድረ-ገፅ በመምራት ለጥቃቱ ማስፈጸሚያ የታጩ አካላት ሚስጥራዊ መረጃዎን እንዲሰጡ የተለያዩ የማሳመኛ መንገዶች ይጠቀማሉ።
የዚህ አጥፊ ተለእኮ ካነገቡ መካከልም ስፓሞች፣ ፊሺንግ ኢ-ሜይሎች እንዲሁም ሀሰተኛ ድረ-ገፆች ዋነኛ መገኛ ሆነዉ እናገኛቸዋለን።
ነገር ግን አጥፊ ተልእኮ ያነገቡ ማስፈንጠሪያዎች (Links) በሐሰተኛ እና ሕጋዊ (Legitimate) ድረ-ገፆች ላይ ሊፈጠሩ ወይም ሊገኙ እንደሚችሉ ማስተዋል አስፈላጊ ነው።
ስለሆነም አጥፊ ተልእኮ ያነገቡ አገኛኖች ወይም ማስፈንጠርያዎች (Links) የሳይበር ወንጀለኞች ሳይበር ጥቃት ለማድረስ የሚስችሏቸው ውጤታማ መንገድ ሆነዉ አግኝተዉታል።
በአደገኛ ተልእኮ ባላቸዉ ሊንኮች የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዉስጥም የሚከተሉትን ይገኙበታል፦
#የማንነት_ስርቆትን ወይም ሌሎች የማጭበርበር ተግባራትን ለመፈጸም
#_የግል_ሚስጥራዊ መረጃዎችን ወይም አካዉንቶችን መለያዎችን ለመደረስ #access ለማድረግ
#_አደገኛ_ተልእኮ ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን ለማውረድ
#_በራምሶምዌር አማካኝነት ፋይሎች ለምምስጠር ወይም ለመቆለፍ
#_በርቀት ሆነዉ ያልተፈቀደላቸዉን ስርአተ ኮምፒዉተር ለመቆጣጠር እና ለመበርበር።