askwala.com - የራድዮሎጂካል እና ኒኩሊየር አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ ስራ በኢትዮጵያ
Header







የራድዮሎጂካል እና ኒኩሊየር አደጋ ዝግጁነት እና ምላሽ ስራ በኢትዮጵያ


1. የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን የሚያከናውነው የራዲዮሎጂካል እና ኒኩሊየር ድንገተኛ አደጋ ዝግጁነት ምላሽ ስራዎች፤
-----------------------------------------------------------------------
እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎችንና ቁሶችን ይቆጣጠራል፤ይከታላል፡፡ የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎችንና ቁሶች ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ፤ ከሀገር ሲወጡ፤ ጥቅም ላይ ሲውሉ፤ ሲጓጓዙ፤ ሲወገዱ፤ ሲዘዋወሩ፤እና ሌሎች ተዛማጅ ስራዎች ሲከናወኑ የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን ያከናውናል፤ ህግ የማስፈጸም ስራ ይሰራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የራድዮሎጂካልና ኒኩሊየር አደጋ ሲከሰት ተገቢነት ያለውና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የዝግጁነት ስራ በመስራት ምላሽ ሚሰጥ ተቋም ነው፡፡
የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን ብሄራዊ የራድዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋ ምላሽ ለመስጠት የሚያችሉ መስፈርቶችን፤ እቅዶችን፤ የስራ ቅደም ተከተሎችን፤ እና መምሪያችን ያዘጋጃል ቀጣይነታቸውንም ይከታላል፤ የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎችንና ቁሶችን ቆጠራ ያካሂዳል፡፡
2. የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ ስንል ምን ማለታችን ነው?
------------------------------------------------------
i. የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር እክል (Radiologiical or Nuclear Accident):- ማለት ማንኛውም ሳይታሰብና ሳይታቀድ በመሳሪያ ብልሽት፤ በሰዎች ስህተት፤ እና በመሰል ሁኔታዎች ሊከሰት የሚችል የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ ሆኖ ከደህንነት አንጻር ግን ችላ ሊባል የማይችል እክል ወይም አደጋ ነው፡፡
ii. የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ (Radiologiical or Nuclear Emergency):- ይህ የአደጋ አይነት በሰው ጤና፤ በንብረት፤ በአካባቢና በህይወት ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ታሳቢ ባደረገ መልኩ አደጋውን ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት ፈጣን ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ወይም የሚያስፈልገው የአደጋ አይነት ነው፡፡
የራድየሽን አመንጭ መሳሪያዎች ወይም ቁሶች በኢንዱስትሪው፤ በግብርናው፤ በምርምርና ጥናት፤ በጤናው ብሎም ሀይል ለማመንጨት ያላቸው ሚና ከጊዜ መደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የአደጋው መጠንም በዚሁ ልክ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ የራድየሽን አመንጭ መሳሪያዎች ወይም ቁሶች በመጠቀም ሀይል በሚያመነጩ (NPPs) ወይም የምርምር ጣቢያዎች (Research Reactors) ከሚደርሰው አደጋ ይልቅ በሌሎች ዘርፎች የሚደርሰው አደጋ የበዛ ነው፡፡
3. የራዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ ምድቦች (Categories Of Radiological & Nuclear Emergency)
------------------------------------------------------------------------
የራዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ በዋናት በአምስት ምድቦች ይመደባል እነሱም፡-
ምድብ I (Category II) ፡- በዚህ ምድብ የሚካተተው የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ በዋናነት በኒኩሊየር ማብላያዎች ወይም በሀይል ማመንጫ የኒኩሊየር ፓዎር ፕላንቶች እና ሪሰርች ሪአክተሮች ይከሰታል፡፡ በዚህ ምድብ የሚካተት አደጋ በተማት እና ከተማት ውጭ የከፋ የጤና ችግር (ከከፋ የአካል ጉዳት እስከሞት የሚያደርስ) የሚያስከትል ሲሆን የሚያመነጨው የሀይል መጠንም (Power level) ከ100MW ይበልጣል፡፡
ምድብ II (Category II) ፡- በምድብ II የሚካተተው የራድዮሎጂካል ወይም ኒኩሊየር አደጋ በዋናነት ሃይል የማመንጨት አቅማቸው ከ 2MW እስከ 100MW ድረስ ማመንጨት ከሚችሉ የጨረራ አመንጭ ቁሶች፤ መሳሪያዎች ወይም ተቋማት ነው፡፡
ምድብ III (Category III) ፡- በዚህ ምድብ ሊካተት የሚችል የኒኩሊየር ወይም ራድዮሎጂካል አደጋ ሲከሰት አደጋ በደረሰባቸው ተቋማት ውስጥ የጨረራ የውስድ መጠንን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ የዚህ ምድብ የራድዮሎጂካል ወይም የኒኩሊየር አደጋ በዋናነት ሃይል የማመንጨት አቅማቸው እስከ 2MW ድረስ በሆኑ ሪአክተሮች ይከሰታል፡፡
ምድብ IV (Category IV) ፡- በዚህ ምድብ ሊካተቱ የሚችሉ የራዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋዎች በሀገራት የመግቢያና መውጫ ጠረፎች፤ የአየር ማረፊያዎች፤ የባህር በሮች፤ በብረታብረት ማቅለጫ እና ማከማቻ ቦታዎች ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ምድብ ሊካተት የሚችል ማንኛውም የራድዮሎጂካል ድንገተኛ አደጋ ሲከሰት አፋጣኝ የሆነ የመከላከል እርምጃ መውሰድ ለአላስፈላጊ የጨረራ የውስድ መጠን መጋለጥን ይቀንሳል፡፡ 

















Short info

× Chat