ኒውራልሊንክ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ በሚቀበር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማይክሮቺፕ አማካኝነት ኮምፒዩተር እና ተያያዥ ማሽኖችን ያለእጅ ንክኪ በአዕምሮ ብቻ የማዘዝ አቅምን ይሰጣል፡፡
ቴክኖሎጂው በተለያየ ምክንያት ሙሉ ሰውነታቸውን ማንቀሳቀስ ለማይችሉ ሰዎች ስማርት ስልኮቻቸውን እና ተያያዥ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ ያስችላል ሲል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡
በአዕምሮ የሚቀመጠውን ማይክሮቺፕ ገመድ አልባ በሆነ ሁኔታ የኃይል ሙሌት (ቻርጅ) ማድረግ የሚቻል እና ምቾት የማይነሳ መሆኑን የኩባንያው መስራች ኤለን መስክ በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል፡፡
ኩባንያው በሰው ላይ ሊያደርግ ላቀደው የመጀመሪያ ሙከራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ለማሟላት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን ዘገባው አመላክቷል፡፡