askwala.com - ሜታ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተቀመር አስተዋወቀ፡፡
Header







ሜታ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተቀመር አስተዋወቀ፡፡

Image name: Data2vec.jpg

በቅርቡ ስያሜውን ወደ ሜታ የቀየረው የቀድሞው ፌስቡክ ኩባንያ ለሁለገብ አገልግሎቶች መዋል የሚችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተቀመር አስተዋወቀ፡፡
#Data2vec የሚል መጠሪያ የተሰጠው ስልተቀመር በሰዎች ምደባ (label) ካልተደረገባቸው የምስል፣ የድምፅ እና የጽሁፍ ዳታ እራሱን የማስተማር አቅም እንዳለው ኒውስዊክ ዘግቧል፡፡
ከሰዎች ክትትል ውጭ እራሱን ማስተማር የሚችለው ይህ ስልተቀመር በኩባንያው ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ አስደሳች ግኝት ተብሎ ተሞካሽቷል፡፡
ከዚህ ቀደም በተለያየ መልክ ሲበለፅጉ የቆዩ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ስልተቀመሮች ከሰዎች በሚያገኙት ዳታ አማካኝነት የሚሰለጥኑ እና ውስን አገልግሎቶችን ለመስጠት ይውሉ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በማርክ ዙከርበርግ ትንበያ መሠረት መሰል ስልተቀመሮች ሰዎች በዕለት ከዕለት ሕይወታቸው ለሚከውኗቸው የተለያዩ ተግባራት ውጤታማነት አጋዥ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡
ስልተቀመሩ ወደፊት አካባቢያቸውን ያለማንም እርዳታ እና ችግር መማር የሚችሉ ማሽኖችን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያፋጥን ተነግሮለታል፡፡ 

















Short info

× Chat