askwala.com - በዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡
Header







በዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡


የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) የአንድ አካባቢን የግብርና መረጃ እና እውቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራው ሥራ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ይጠቀማል፡፡ በማሽን ለርኒንግ አማካኝነት የአፈር እና የውሃ አካላትን ሁኔታ፣ አየር ንብረቱን፣ ከዓሣ ምርት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን፣ የእንስሳት እርባታ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን ያጠናል፡፡
ፋኦ በዚህ ረገድ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ዋፖር (WaPOR) ተጠቃሽ ነው፡፡ ዋፖር ሳተላይት ወይም ሌሎች የሪሞት ሴንሲንግ መንገዶችን በመጠቀም በአፍሪካ ለግብርና መዋል የሚችሉ የዉሃ አካትን ሁኔታ በመከታተል ሰፊ መረጃን ይሰበስባል፡፡
እንደ አናሊቲክስ ኢንሳይት ሀተታ በዚህ መንገድ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት አማካኝነት በመተንተን ለተለያዩ ሰብሎች እና አካባቢዎች ውጤታማ የሆነውን የውሃ አጠቃቀም ያመላክታል፡፡ መረጃውንም በድረ-ገጹ ተደራሽ ያደርጋል፡፡
ድርጅቱ በተመሳሳይ መልኩ የውሃ እጥረት እና ድርቅ ሊከሰትባቸው የሚችሉ አካባቢያዊ አዝማሚያዎችን ለመለየት Agricultural Stress Index (ASIS) የተባለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት በተግባር አውሏል፡፡
ፋኦ ርሀብን ለማጥፋት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ እንዲሁም የተመናመኑ የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ቴክኖሎጂው ትልቅ እገዛ እያደረገ ነው፡፡ 

















Short info

× Chat