askwala.com - ኮምፒውተሮች በእጅ ምልክት ብቻ እንዲታዘዙ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮግራም እየበለጸገ ነው፡፡
Header







ኮምፒውተሮች በእጅ ምልክት ብቻ እንዲታዘዙ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮግራም እየበለጸገ ነው፡፡


በመደበኛ ኮምፒውተር ሊተገበር የሚችለው እና ወደ ምስለ ምርት ደረጃ የተሸጋገረው ይህ ፈጠራ ወደ ኮምፒውተራችን ኪቦርድ እጃችንን በማስጠጋት በምናሳየው ምልክት የተሰጠውን ትዕዛዝ በተማረው መሰረት የሚፈጽም ነው፡፡
"Typealike" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ፕሮግራም ለምሳሌ የቀኝ እጅ አውራ ጣት ወደ ኪቦርዱ ከተመላከተ የሚረዳው ተጠቃሚው የኮምፒውተሩ ድምጽ እንዲጨምርለት እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የሚደረጉ የእጅ እንቅስቃሴዎች እና ምልክቶች ከፕሮግራሙ ተናቦ የኮምፒውተር አጠቃቀማችንን የበለጠ ቀላል እና ተወዳጅ ለማድረግ የመጣ መላ ስለመሆኑ ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል፡፡
በማሽን ለርኒንግ እውን የሆነው ይህን ፕሮግራም ለማበልጸግ ተመራማሪዎቹ የበጎ ፈቃደኞችን የእጅ እንቅስቃሴ እና ምልክት በመቅረጽ አስተምረውታል፡፡
በአሜሪካ የወተርሉ የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ቤት ተመራማሪዎች እውን የሆነው ይህ ፕሮግራም ኮምፒውተሮችን በማውዝ እና ሾርትከት የማዘዙ ሂደት ወደፊት እየቀረ እንዲመጣ ለማድረግ በማሰብ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡
የዘገባው ምንጭ ሳይንስ ዴይሊ እንዳተተው ፈጠራው ከዚህም በላይ የኮምፒውተር አጠቃቀማችንን ቀላል እና ተወዳች የሚያደርጉ መተግበሪያዎችን እያካተተ እንደሚሄድ አስነብቧል፡፡ 

















Short info

× Chat