askwala.com - በሕንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትን ለመከላከል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የመጠቀም እቅድ
Header







በሕንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነትን ለመከላከል አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የመጠቀም እቅድ


የሕንድ መንግሥት በስርጭት ወቅት የሚገጥመውን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ብክነት ለመግታት የሚያስችል አማራጭ እንዲያቀርቡ በሃገሪቱ ለሚገኙ ጀማሪ የቴክኖሎጂ አልሚ ተቋማት ጥሪ አቀረበ፡፡
ጥሪ የቀረበላቸው የቴክኖሎጂ አገልግሎት ሰጪዎች በኃይል አቅርቦት እና ስርጭት ሂደት ያለውን ዳታ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ማሽን ለርኒንግ፣ ብሎክ ቼን እና የኢንተርኔት ኦፍ ቲንግስን በመጠቀም እንዲተነትኑ እና መፍትሔ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል፡፡
የሚተነተነዉ ዳታ እና የሚቀርበዉ የመፍትሔ አማራጭ የተጠቃሚዎችን የኃይል ፍጆታ ለመለካት፣ በየአካባቢው ያሉ የኃይል አስተላላፊዎች እና መጋቢዎችን ለመከታተል ጥቅም ላይ እንደሚውል ዘ ኢኮኖሚክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
ሀገሪቷ በኃይል ስርጭት ወቅት ብክነት ከሚገጥማቸው የዓለማችን ሀገራት ቀዳሚ መሆኗ ይነገራል፡፡ ይህ ችግር በአጠቃላይ የኃይል ዘርፉ አዋጭነት ላይ ከፍተኛ ተግዳሮት በመደቀኑ መንግስት መፍትሔ ለመሻት መገደዱን ዘገባው አትቷል፡፡
በሕንድ በዓመት በአማካይ ሃያ በመቶ የሚሆን ኃይል በስርጭት ወቅት እንደሚባክን በዘገባው ተገልጿል፡፡ 

















Short info

× Chat