askwala.com - 82 ከመቶ የህዝበ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸዉ መተግበሪያዎች የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት አለባቸዉ፡ ጥናት
Header







82 ከመቶ የህዝበ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙባቸዉ መተግበሪያዎች የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት አለባቸዉ፡ ጥናት


ከአምስት የህዝብ አግልግሎት ሰጪዎች ከሚጠቀሙባቸው መተግበሪያዎች መካከል ከአራት በላይ የሚሆኑት (82 ከመቶ) የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት እንዳለባቸዉ የቬራኮድ (Veracode) ጥናት ይፋ አደረገ።
ይህ ተጋላጨነት መጠን ከሌሎች ሴክተሮች አንጻር በጣም ከፍተኛዉ የሚባል የሳይበርር ጥቃት ተጋላጭነት መሆኑን በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ላይ የተሰማራዉ “ቬራኮድ” ኩባንያ በጥናቱ ጠቁሟል።
ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች ጋር ሲነጻጸር ለመንግስት አገልግሎት ሰጪ ሴክተሮች ጥቅም ላይ የዋሉ መተግበሪያዎች ላይ የተገኙ ክፍተቶችን ለመጠገን በእጥፍ የመጠገኛ ጊዜ እንደሚጠይቅ ነዉ ተመራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት።
ከዚህ ባሻገር 60 በመቶ የሚሆኑት ህዝብ ቤተ-መጽሃፍት ላይ የሚገኙ ክፍተቶች ሳይጠገኑ እስከ ሁለት አመት እንደሚቆዩም የተገለጸ ሲሆን ይህ ጊዜም ከሌሎች ሴክተሮች አንጻር ሲታይ እጥፍ ጊዜያት እንደሚቆይ እና ከአጠቃላይ ሲታይ ደግሞ እስከ 15 ወራት የተራዘመ ጊዜ እንደሚጠይቅ ታዉቋል።
ይህንን የጥናት ሪፖርት ሲዘጋጅ በህዝብ አገልግሎት መስጫ ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣በፋይናንስ አገልግሎቶች ፣በችርቻሮ እና ሆቴል ፣ በጤና አጠባበቅ እና በቴክኖሎጂ ክፍለ ኢኮኖሚ ዉስጥ ተግባራዊ ከሆኑ ግማሽ ሚሊዮን መተግበሪያዎችን ከ20 ሚሊዮን በላይ መረጃዎች ላይ በመንተራስ የተዘጋጀ እንደሆነ ቬራኮድ ጠቁሟል።
የቬራኮድ ዋና የምርምር ኦፊሰር የሆኑት ክሪስ ኢንግ፣ በህዝብ አገልግሎት ዘርፍ ላይ በሃላፊነት ያሉ እና ፖሊሲ የሚያወጡ አካላት ጊዜያቸዉ ያለፈባቸዉ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች እና ከፍተኛ የህዝብ ሚስጠራዊ መረጃ የያዙ መተግበሪያዎች በመረጃ መዝባሪዎች ቀዳሚ ኢላማ መሆናቸዉን ሊገነዘቡ እና የማስተካከያ ርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ብለዋል። 

















Short info

× Chat