የቢዘነስ ኢ-ሜይል ጥቃት አድራሾችን ለማደን ኦፕትሬሽኑ በመስከረም ወር/2021 እ.አ.አ የተጀመረ ሲሆን የአሜሪካዉ የፍትህ ቢሮ እና አለም አቀፉ የህግ አስከባሪ አካላት በጥምረት የተካሄደ መሆኑ ታዉቋል።
ኦፕሬሽን ኤግል ስዊፕ (Operation Eagle Sweep) በሚል በተካሄደዉ ወንጀለኞችን የማደን ዘመቻ በሶስት ወራት ዉስጥ ብቻ 65 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቋማት ላይ የኢ-ሜይል ጥቃት አድርሰዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ መሆናቸዉ ተጠቁሟል።
በጥምረቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል ከናይጄሪያ 12፣ ከደቡብ አፍሪካ ስምንት ፣ ከካናዳ ሁለቱ እና አንድ ደግሞ ከካምቦዲያ ሲሆኑ በተመሳሳይ ጊዜ በአውስትራሊያ፣ በጃፓን እና በናይጄሪያ የሚገኙ ፖሊሶች የቢዝነስ ኤ-ሜይል ጥቃት አድርሰዋል ብለዉ የጠረጠሯቸዉን ግለሰቦች የመያዝ ዘመቻዎችን ማከናወናቸዉ ተገልጿል።
እንደ የአሜሪካዉ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (FBI) ሪፖርት ባለፈው በፈረንጆቹ 2021 ዓመት በቢዝነስ ኢ-ሜይል አማካኝነት በተሰነዘረ የሳይበር ጥቃት 2.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ተቋማትን ያስወጣ ሲሆን ይህ መጠን ከ2020 ዓመት ከደረሰዉ ኪሳራ ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ቢሊዮን ዶላር አድጓል።
በተያያዘም ከአጠቃላይ የሳይበር ወንጀል ኪሳራ ውስጥ በቢዝነስ ኢ-ሜይል የሚደርስ ጥቃት አንድ ሶስተኛውን እንደሚሽፍን ተጠቁሟል።
የንግድ ኢ-ሜይል ጥቃት የፋይናንስ ዘረፍን በከፍተኛ ደረጃ ለጉዳት ከሚዳርጉ የበይነ-መረብ የቀጥታ ጥቃቶች መካከል አንዱ ሲሆን ብዙዎቻችን የግል ኢ-ሜሎቻችንን ለተቋማዊ አገልግሎት ስለምንጠቀም ከመረጃ መንታፊዎች እና ከህገ-ወጥ ተልኮ ማስፈጠሚነት እንድንታደግ ይጠበቃል፡፡